ሊዮ ሜሲ የዣቪን ሬከርድ ተስተካከለ

ሊዮ ሜሲ የዣቪን ሬከርድ ተስተካከለ

ሜሲ ሁዌስካ ላይ 2 ባገባበት ምሽት የዣቪ ኸርናንዴዝን ለባርሤሎና ያደረጋቸውን 767 ጨዋታዎች ሬከርድ እኩል ማድረግ ችሏል። ባርሳም በጨዋታው 4-1 ሲያሸንፉ ቀሪዎቹን ግቦች ግሪዝማን እና ሚንጌዛ አስቆጥረዋል ።
የ33 አመቱ አርጀንቲናዊ ምናልባትም የአመቱ ምርጥ ጎሉ የሆነ ጎልን ሲያስቆጥር ግብ የሆነ ኳስንም አመቻችቶ አቀብሏል።በአጠቃላይ ዘላቂ ብቃቱን አስመስክሯል ለ13 ተከታታይ የውድድር አመቶችም 20 የላሊጋ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።


ባርሳ ባለፉት 12 ጨዋታዎች 11 አሸንፎ 1 አቻ በመውጣት ላሊጋው ላይ ጠንካራ ፉክክር እያደረጉ ነው ከመሪው አትሌቲኮ በ4 ነጥብ ነው ዝቅ ሚሉት ከነሱም ጋር በግንቦት ጨዋታ አላቸው። እሁድ ከሪያል ሶሴዳድ ሲጫወቱ ሜሲ የዣቪን ሬከርድ 768 በማድረግ ይሰብራል ብዙ ተጫዋቾችም እንኳን ለዚህ አበቃ ሲሉት ራሱ ዣቪ አንደኛው ነው ካርለስ ፑዮል፣ አንድሬስ ኢንየሽታ ፣ ቡስኬትስ ፣ ሉዊስ ስዋሬዝ ፣ ኔይማር እና ጄራርድ ፒኬ በቪድዮ መልክታቸውን ካስተላለፉለት መሀል ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.