ኤቨርተኖች የአንፊልዱን ገድል ይደግሙታል ?
ኤቨርተኖች የአንፊልዱን ገድል ይደግሙታል
በሰኞ ምሽት ጨዋታ ኤቨርተኖች በጉዲሰን ፓርክ ከታሪካዊው የአንፊልድ ድላቸው በኋላ ሳውዝሀምፕተንን ያስተናግዳሉ፡፡ኤቨርተን እና ደጋፊዎቻቻቸው ድርብርብ ደስታ ላይ ናቸው የባለፈው ሳምንት ድል ላይ የአዲስ እስታዲየም ግንባታ ፍቃዳቸው መጽደቁም ጭምር ነው፡፡ ሉካስ ዲኜም ከክለቡ ጋር ሚያቆየውን የረጅም ጊዜ ኮንትራት ፈርሟል፡፡የባለፈው ሳምንት ድል ከላይ ሚቀመጡት 4ቱ ውስጥ የመጨረስ ተስፋቸውን አለምልሞታል ፡፡መቅረፍ ያለባቸው ነገር በሜዳቸው ነጥብ ሚጥሉት ዋጋ እያስከፈላቸው ነው፡፡በዘንድሮ የውድድር አመት ቡድኖች ሁሉም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ከሜዳቸው ውጪ ሲሆን ነው የተሻለ ነጥብ እያገኙ ያሉት በተለይ ደግሞ ኤቨርተን በሜዳቸው 5 ጨዋታ አድርገው 4ቱን ተሸንፈዋል እሱንም ለወራጅ ቀጠና ከሚፋለሙት ኒውካስትል እና ፉልሀም ተጋጥመውም ተሸንፈዋል ፡፡ ካርሎ አንጮሎቲም የታክቲክ እውቅ መሆናቸውን ከሊቨርፑል በነበረው ጨዋታ ያሳዩ ሲሆን ያንኑ አይነት መፍትሄ በሜዳቸው ለሚያረጓቸው ጨዋታዎች መፈለግ አለባቸው ፡፡
ተጋጣሚው ሳውዝሀምፕተን በአንጻሩ ደካማ አቋም እያሳየ ሲሆን የራልፍ ሀስንሁትል ቡድን ከዚህ ቀደም ግንኙነታቸው በተሻለ ታክቲክ 2-0 ማሸነፍ ችለው ነበር የአመቱ መጀመሪያ ላይ ሊቨርፑልን ካሸነፉ በኋላ ግን ባደረጉዋቸው 8 ጨዋታዎች 7ቱ በሽንፈት ሲጠናቀቁ አንድ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት፡፡
ሳውዝ ሃምፕተን ብዙ ተጫዋቾቹን በጉዳት እንዳጣ ይታወቃል ኦሪዮ ሮሚዩ ፤ ሚናሚኖ ፤ በደናሬክ የመሳሰሉ ተጫዋቾች ይጠቀሳሉ በኤቨርተን በኩል ደግሞ ዶሚኒክ ካልቨር ሌዊን እና አለን ወደ ሜዳ ሲመለሱ የሪ ሚና እና ፊሊፕ ግባሚኒ በጉዳት አይገኙም፡፡
የኤቨርተኑ አለቃ ስለጨዋታው በኔ አስተሳሰብ የደረጃ ሰንጠረዡን ማየት የለብንም ጨዋታ በጨዋታ እያለፍን ራሳችንን የውድድር አመቱ መጨረሻ ላይ ማየት ነው ሲሉ በአውሮፓ መድረክ መጫወትም ትልቁ ህልማቸው መሆኑንም አልደበቁም ለክለቡም ሆነ ለተጫዋቾቹ አንድ እርምጃ ወደፊት ማለትም ነው ብለዋል፡፡
የሳውዝሀምፕተኑ የራልፍ ሀስንሁትል ደግሞ የባለፈው ጨዋታችን ጥሩ ነበር አሁን ግን ዕዛ አቋም ላይ አደለንም ኤቨርተን ደግሞ የተሸለ አቋም ላይ ነው ብለዋል፡፡በቻልነው አቅም ጥሩ ውጤት ይዘን ከሜዳ ለመውጣት እንሞክራለን ብለዋል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጉዲሰን ፓርክ ከምሽቱ 5፡00 ይደረጋል