ሶልሻየር በዳኞች ላይ ወቀሳውን አሰማ
ሶልሻየር በዳኞች ላይ ወቀሳውን አሰማ
በጨዋታው ካሉም ሆድሰን ኦዶይ ፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ በእጁ ኳስ የነካበትን አጋጣሚ በንዴት ገልጸዋል የኛ ተጫዋች ነው የነካው ብለው ሲጮሁ ነበር ቪዲዮውን ስታየው ግን እኛ ሁለት ነጥብ ተነጥቀናል ሲል ምሬቱን ገላጿል ቡድኑም ከመሪው ማንችስተር ሲቲ በ12 ነጥብ ዝቅ ብሎ እሁድ እለት ተጠባቂ ጨዋታውን ከከተማ ተቀናቃኙ 20 ጨዋታዎችን ተከታታይ ካሸነፈው ማንችስተር ሲቲ ያደርጋል፡፡
የጨዋታው የመሀል ዳኛ ስቱዋርት አትዌል በእጅ ተከክቷል የተባለውን ኳስ በቫር አይተውም ውሳኔያቸው ያው ነበር ፍጹም ቅጣት ምቱን አልሰጡም፡፡አሰልጣኝ ሶልሻርም ሲጠየቅ 100 በ 100 ፔናሊቲ ነበር በተቃራኒ ተጫዋቾች ግፊት ነው ያልተሰጠን እየተጯጯሁ ብሏል፡፡ይህም ነገር ተደጋጋሚ እየሆነ ነው ከሁለት ሳምንታት በፊትም ከዌስት ሀም ጋር አቻ በወጡበት ጨዋታም የፍጹም ቅጣት ምት ተከልክለዋል ይህም በሚድያዎችም ሆነ በተለያ አካላት ማንችስተር ዩናይትድ ብዙ የፍጹም ቅጣት ምት ያገኛል እየተባለ ለረጅም ጊዜያት ሚነሳው ሀሳብ ዳኞች ላይ ተጽእኖ ሳያሳድር አይቀርም ይባላል የአሰልጣኙም ሀሳብ እሱነው፡፡
ስለጨዋታው ሶልሻር በሰጠው ሌላኛው አስተያት ቡድኑ ተጭኖ ለመጫወት መሞከሩን እና ግን በቂ እንቅስቃሴ እንዳላረጉ እና 1 ነጥብ ብቻ መውሰድ እንዳልነበረባቸው አንስቷል ቡድኑ ከትላልቆች 6 ቡድኖች ጋር ሲጫወት ጎል የማስቆጠር ችግር ተደጋጋሚ ጊዜ ታይቶበታል በዘንድሮ የውድድር አመት ከነዚህ ቡድኖች ጋር 7 ጨዋታ አድርጎ አንድ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው ግብ ያስቆጠሩት እሱንም በቶተንሀም 6-1 ሲሸነፉ፡፡በዚህም ላይ ሀሳብ የሰጡት አሰልጣኙ አውቃለው ብዙ ጎል የለንም ለዚህም ነው ወደ መገባደጃው ላይ ተጨዋቾች ተጭነው እንዲጫወቱ ምገፋፋው ግን ያው ከትላልቆቹ ጋር መረባችንን አናስደፍርም እሱም ይመስገን ሚያስብል እና ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡
በተቃራኒው ቶማስ ቱሄል ይሄ ሁሉ ግርግር አያስፈልግም ነበር የነሱ ተጫዋች ነክቶ ለፔናሊቲ ቫር ማየት አያስፈልግም ነበር ዳኛው ልክ ነበር ማየትም አይጠበቅበትም ነበር እንኳን ብቻ ፔናሊቲ አልሆነ እሱ አስከፊ ነበር ሚሆነው፡፡ ጨምረውም በቡድናቸው ከኳስ ውጪ እንቅስቃሴ ደስተኛ እንደሆኑ ገልጻዋል ሆኖም ዌስት ሀምን መብለጥ እና የቻምፒየንስ ሊግ ተርታ ውስጥ መግባት ሚችሉበትን እድል ስላመከኑ እሱ አስቆጭቷቸዋል ቢሆንም ግን ባለፈው ወር ክለቡን ከያዙ ጀምሮ ባደረጓቸው 9 ጨዋታዎች ሽንፈትን አላስተናገዱም፡፡
ሁለቱ ክለቦች በቀጣይ ከባድ ተጋጣሚዎች ናቸው ሚጠብቋቸው ችልሲ በአንፊልድ ሃሙስ እለት ሊቨርፑልን ይገጥምና ቀጣይ ሳምንት ኤቨርተንን ያስተናግዳል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ እረቡ ከክሪስታል ፓላስ እሁድ ከማንችስተር ሲቲ ከዛም ቀጥሎ ያሏቸው ጨዋታዎች ከዌስትሃም እና በኤፍ ኤ ካፑ ከ ሌስት ሲቲ ነው በመሃልም ኤሲሚላንን ይገጥማሉ በዩሮፓ ሊግ፡፡