የኢሮፓ ሊግ ድልድሎች ይፋ ሆኑ
የኢሮፓ ሊግ ድልድሎች ይፋ ሆኑ
በኢሮፓ ሊግ ምድብ ድልድል ማንችስተር ዩናይትድ ከኤሲ ሚላን የተደለደሉ ሲሆን የድሌድሉ ሁሉ ከባድ ጨዋታ እንደሆነ ታምኖበታል የዝላታን ኢብራሂሞቪች የቀድሞ ክለቡን መግተም ደግሞ ጨዋታውን ተመባቂ ያረገዋል፡፡
አርሰናል በበኩሉ ጥሎ ማለፉን በአስጨናቂ ሁኔታ አልፎ የመጣ ቢሆንም ለዋንጫው እንደሚታገል ግልጽ ነው በእጣ አወጣጡም በተመሳሳይ ሰአት ባለፈው የዩሮፓ ሊግ ውድድር ዘመን ከውድድር ያሰናበቷቸውን ኦሎምፒያኮሶች ይገጥማሉ ፡፡
ቶተንሀም በበኩሉ ዳይናሞ ዛግሬብን ይገጥማል፡፡የጆዜ ሞሪንሆው ቡድን ለካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜም መድረሱ ቡድኑ በውድድር ዘመኑ ዋንጫ ሚያነሱበት እድል ሰፊ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በሌሎች ድልድሎች
ሬንጀርስ – ስላቪያ ፕራ
አያክስ – ያንግ ቦይስ
ዳይናሞ ኪቭ – ቪላሪያል
ሮማ – ሻካታር ዶኔትስክ
ግራናዳ – ሞልደ
ሆነው የተደለደሉ ሲሆን የ16 የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች 1ኛ ዙር ግጥሚያዎች መጋቢት 2 ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ መጋቢት 9 ይደረጋሉ፡፡