ማንችስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
ማንችስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
ትናንት ከሪያል ሶሴዳድ ጋር በመልስ ጨዋታ 0-0 በመለያየታቸው በድምሩ 4-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ቀጣዩን ዙር መቀላቀል የቻለው በጨዋታው ሁለቱም ክለቦች የማግባት እድሎችን ፈጥረው ነበር፡፡በመጀመሪያው ጨዋታ ሶሴዳዶች ደካማ እንቅስቃሴን ቢያሳዩም በመልሱ ጨዋታ ተሻሽለው ተገኝተዋል፡፡ጨዋታቸው ፉክክር የበዛበትነበር ሶሴዳዶችም የፍጹም ቅጣት ምት በ13ኛው ደቂቃ በኦያሪዛባል ስተዋል ፈጹም ቅጣት ምቱም ዳንኤል ጄምስ ከሁዋላ አንዶኒ ጎሮሳቤል ላይ በሰራው ጥፋት ነው፡፡
በማንችስተር ዩናይትድ በኩል የአንቶኒ ማርሻል ግብ ጠባቂው አሌክስ ሬሚሮ የመለሰበት ሙከራ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ የግብ ቋሚው የመለሰበት ኳስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ባሪያል ሶሴዳድ በኩልም ሳግናን የግብ ቋሚ የግንባር ሙከራውን መልሶበታል፡፡
አግዜል ቱዋንዜቤ ከአሌክስ ቴሌዝ ያገኘውን ኳስ በ63 ደቂቃ ከመረብ ማገናኘት ቢችልም የቡድን አጋሩ ሊንዶልፍ ጆን ባቲስታ ላይ ጥፋት መስራቱ በቫር ቴክኖሎጂ በመረጋገጡ ተሽሯል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድ በአስተማማኝ መልኩ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ሲያረጋግጥ አርብ እለት የእጣ ድልድሉ ሲታወቅ ቀጣይ ተጋጣሚውን ይለያል፡፡