የዋልያዎቹ አሰልጣኝ የሰኞውን ጨዋታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
የሱዳኑ ጨዋታ ከ ዛምቢያው ጨዋታ እንደሚለይ እና በነገው ጨዋታ የቡድኑን 70 ወይም 80 በመቶ ቡድናቸዉን የሚለዩበት እንደሚሆን የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ ፡፡
ሰኞ ወደ ኒጀር ጉዞ የሚያደርገው ብሄራዊ ቡድኑ 23 ተጫዋቾችን ይዞ ከተመረጡት 26 ተጫዋቾች 3ቱ የተቀነሱ ሲሆን ያም ሆኖ ማለትም የሚቀነሱትም የቡድኑ አባል ሆነው ይቀጥላሉ ።
የካፍ አካዳሚ እንደሆቴል ምቹ አይደለም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመሆኑ ተጨዋቾቹ እሱን መታገላቸው በራሱ ያስመሰግናቸዋል ያሉት አሰልጣኙ አክለዉም ሙጂብ ቃሲም እና ሱራፌል ዳኛቸው ከጉዳታቸው ጋር ናቸው ፣ ጉዳት ላይ የነበረው አማኑኤል ዮሀንስ እና አቡበከር ናስር ተሽሏቸው ተቀላቅለውናል ብለዋል ፡፡