ዋልያዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምድ አደረጉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለተኛ ልምምዳቸውን ማድረጋቸዉ ታውቋል
በዛሬው ልምምድ ላይ አማኑኤል ዮሐንስ ካጋጠመው መጠናኛ ጉዳት በማገገም ዋናውን ቡድኑን በመቀላቀል ሙሉ ልምምድ ማድረጉ ሲታወቅ ከጥቂት ቀናት በፊት ጉዳት ያስተናገደው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ለብቻው ልምምድ አድርጉኣል ፡፡
ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ልምምዳቸውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሄዱት ዋልያዎቹ የእርስ በእርስ ግጥሚያዎቹ በዛሬው ዕለት ከነበሩ የልምምድ አይነቶች ሲሆን ጠንከር ያለ ልምምዳቸውን ቀጥለውበታል ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው አርብ ከሱዳን አቻቸው ጋር ለመጫወት በተደረገ የኢሜል ልውውጥ የተስማሙ ሲሆን ጨዋታው እንደሚካሄድ ይጠበቃል ስትል ሀትሪክ ስፖርት ዘግባለች፡፡