የሀሪኬን እና ሶን ሁንግ ድንቅ ጥምረት የታየበት የቶትንሀም ሆትስፐርስ ድል

ቶትንሀም ሆትስፐርስ በሁለቱ አጥቂዎቹ ሀሪኬን እና ሶን ሁንግ ሚን ድንቅ ጥምረት በያዝነው የውድድር ዓመት በአያሌው እየተጠቀመ ይገኛል።

በትናንትናው ምሽት የለንደኑ ክለብ በርንሌይን ባሸነፈበት ጨዋታ የተቆጠረችው ብቸኛ ግብም በሁለቱ ጥምረት የመጣች ሲሆን ፣ ሁለቱ ተጨዋቾች በፕሪምየር ሊጉ በ 29 ግቦች ላይ የተጣመሩ ሲሆን ይህም በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ሁለተኛው ብዙ ግብ ላይ የተሳተፈ ጥምረት መሆን ችሏል።

በፕሪምየር ሊጉ የላምፓርድ እና የድሮግባ ጥምረት 36 ግቦች ላይ የተሳተፈ ሲሆን ይህም በውድድሩ ክብረ ወሰን በመሆን መመዝገቡ የሚታወስ ነዉ።

ስፐርስ በርንለይን 1-0 በመርታት በ 11 ነጥብ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ካሉ በኃላ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኬን የወደፊት የሰሜን ለንደን ቆይታው ብሩህ እንደሆነ ተናግሯል።

የሰን ሂዩንግ ሚን የሁለተኛ አጋማሽ ጎል የበርንለይን የተከላካይ መስመር ለመስበር ስታትሩ ለማሹት ለጆሴ ሞሪንሆ ቡድን ሙሉ 3 ነጥብ አስገኝታለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published.