የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አሸናፊ በጋሻው በኢንተረኮንትኔታል ሆቴል እውቅናና ምስጋና ተሰጠው
ቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አሸናፊ በጋሻው
ከ1977 አመተ ምህረት 1991 አመተ ምህረት ድረስ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና ለኢትዮጵያ ቡና ላበረከተው አስተዋጽኦ
ነሀሴ 24 ቀን ከምሽት 12 30 እስከ ምሽት 3 ሰአት በተደረገ ስነስርአት በኢንተርኮኔቲኔታል ሆቴል እውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል።
በዚሁ ፕርግራም ላይ በአስተባባሪዎቹ አማካኝነት
የተሰበሰበ 905 ሺብር ተበርክቶለታል ።
በዚህ የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ላይ በእንግድነት
አቶ ኢሳያስ ኢሳያስ ጅራ የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት
መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ቡና የቦርድ ፕሬዚደንት
አት ክፍሌ አማረ የኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዘዳንት
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የእግር ኳስ ቤተሰቦችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አት ክፍሌ አማረ የቡና የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዘዳንት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል
<<የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የሆነውና ከኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጋር የእድሜ ሲሶውን ያሳለፈው አሸናፊ በጋሻው
የክለቡን ስኬት ለአመታት ከክለቡ ጋር አጣጥሟል ።
ፈተናዎችን እንደተጨዋች ብቻ ሳይሆን እንደባለቤት ተጋፍጧል ለመፍትሄ ሩጧል ዋጋም ከፍሏሎ ታማኝነትን ከቃል በላይ አሳይቷል ልብ ላላቸው አስተምሯል ስለክለብ ፍቅር በሜዳ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ ባለ ህይወቱም ዋጋ ከፍሏል >>
በማለት ስለ አሸናፊ በጋሻው ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን
<< ይህ የአሸናፊ በጋሻው የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም እንዲዘጋጅ ሀሳብ በማመንጨት
ከማህበሩ ጋር በመስራት ፍጹም ፍላጎትና ቅንንነት በማሳየት ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን በመሰዋት አስተዋጽኦ ላደረጉት
ለአቶ ኢሳያስ ደንድር የቀድሞ የኢትዮ ኤሌትሪክ እግር ኳስ ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ
ለአንዋር ያሲን በቀድሞ መብራት ሀይል በኦሜድላ በኢትዮጵያ ቡና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በየመን የተለያዩ ከለበች ተጨዋችና የኢትዮ ኤሌትሪክ አሰልጣኝ የነበረ
አንዋር ሲራጅ ( አንዋር ትንሹ) የቀድሞ መብራት ሀይል የቅዱስ ጊዮርጊስ በየመን የተለያዩ ክለቦች በኦማን ና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች የነበረ
አቶ አብዱራህማን መሀመድ(አቡሸት)
እጅግ ትልቅ ክህሎት የነበረው የእግር ኳስ ተጫዋች የነበረና በጉዳት ካቋረጠ በኻላ የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ ሆኖ እያገለገለ የሚገኝና የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት
አሰልጣኝ ፈቀደ ትጋ በተጫዋችነት በኦሜድላ
በአዲስ አበባ ፖሊስና በተለያዩ ቡድኖች በተጫዋችነት ያሳለፈ አሁን ደግሞ በአሰልጣኝነት እየሰራ የሚገኝ
እንዲሁም
ከውጪም በማስተባበር ጎፈድሚ በመክፈት ና በማሰባሠብ የሰሩትን
ቡዛየሁ ዮሀንስ
ቢኒያም ታናሽ
አንዳርጋቸው ሰለሞን
ጥሪውን በመቀበል አስተዋጽኦ ያበረከቱትንና
ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ የሚዲያ ሽፋን ለሰጡት ሚዲያዎች ለፋና ኤፍ ኤም 98.1 ለስፖርት ዞን
ለኢቲቪ ስፖርት ፕሮገራም
ለዋልታ ቴሌቪዥን
ለናሁ ቴሌቪዥን
ከውጪ አሜሪካ ለሚገኘው ሰንደቅ ሚዲያ
በሙሉ አመሥግነዋል ። >>
በቀጣይ ንግግር ያደረጉት አቶ ኢሳያስ ኢሳያስ ጅራ የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት
<< በዚህ ምሽት በዚህ አዳራሽ ያልተለመደ ነገር እያደረግን ስለሆነ በዚህ ፕሮግራም ላይ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉችሁ በእኔና በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ስም አመሠግናለሁ ።
ከዚህ የምንረዳው አሸናፊ ለኢትዮጵያ ቡና የተጫወተ ቢሆንም ፕሮግራሙን ሲያስተባብሩ
የነበሩት አቶ ኢሳያስ መብራት ሀይልን ነው
የሚመሩት
አንዋር የመብራት ተጫዋች ነበር
ይህ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት ነው ከዚህ ልንማር ይቻላል።
በዚህ አንድ አመት ወደቀልባችን የተመለስን ይመስለኛል ። በዚህ አመት ለክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የእድሜ ልክ የስፖርት ሽልማት ሠጥተናቸዋል።
አስራ አራት ቀን አልሞላም ሰኢድ ኪያርና አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ተቋም ወይም ግለሰብ ጋር የድሮዎችን እያስታወስን ወደፊት ማለም የሚል አጀንዳ ይዘው የዙም ሚቲንግ ነበር።
የነበረው ትናትና ማታ ደግሞ የአቶ ይድነቃቸውን 33 ኛ አመት አስመልክቶ አውስትራሊያና አሜሬካ ከሚገኙ
የስፕፖርት ቤተሰቦች ፕሮግራም አዘጋጅተው
ከ3 ሰአትአስከ 6 ሰአት እዛ ፕሮገራም ላይ ነበር። የነበርነው ዛሬ ደግሞ እንደዚህ አይነት መልካም ነገር እያየን ነው።
ትናንት ለሰሩት ስራ በተለይም በህይወት እያሉ
ማመስገን መቻል በጣም ትልቅ ነገር ነው።
ወደፊትም ወደዚህ ኢንደስትሪ ለመምጣት ለሚያስቡት ትልቅ ተስፋ እየሰጠን እንደሆነ የሚያሳይ ፕርግራም ነው >> ብለዋል።
በተጨማሪም አቶ ኢሳያስ ጅራ አሸናፊ በጋሻው ካፍ የቢ ላይሰንስ ስልጠና ሲጀምር በቅድሚያ እንዲያገኝ እድሉ እንደሚመቻችለት ቃል ገብተዋል።
በቀጣይ ንግግር ያደረጉት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ቡና የቦርድ ፕሬዚደንት
<< ስለ አሸናፊ በጋሻው በዚህ የአንድ ሰአት ግዜ ተናግሮ መጨረስ አይቻልም ቁመቱ ከ160 በላይ የሚሄድ አይመስለኝም ነገር ግን አሸናፊ ከሲ ቡድን እስከ ኤ ቡድን በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ አሳልፏል ።
አሸናፊን ልዩ የሚያደርገው ትሁት ሰው አክባሪ ሁሉንም በእኩል የሚያይ ነው ይሄ ጸባዩ ከሜዳ ውጪ ነው። ወደ ኳስ ሲመጣ የቡና ነብር ነወ ተጫዋቹንም ደጋፊውንም የሚያነቃቃ ነው።
አሸናፊ ሽንፈትን የሚቀበል ተጫዋች አይደለም
ኢትዮጵያ ቡና ካፈራቸው ወኔ ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው።>> በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመቀጠልም የአሸናፊ በጋሻውን የእግር ኳስ ህይወት የሚያሳይ ዘጋቢ ቪዲዮ ለተጋባዥ እንግዶች ቀርቧል።
በመጨረሻም ፕሮግራሙን በመምራት ባማረ መልኩ ሲያቀናበሩት በነበሩት ጋዜጠኛ ሰኢድ ኪያርና አሽናፊ ዘለሌ አማካኝነት ዝግጅቱን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት በክብር እንግዶቹ በኩል የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል ።