ዛሬ የተሰሙ የዝውውር ዜናዎች

ዛሬ ጠዋት The Sun እንዳስነበበው ከሆነ የቶትንሀሙ አማካይ ሀሪ ዊንክስ በማንችስተር ሲቲ ቤት እንደሚፈለግ የተነሳ ሲሆን ቶትንሀምም ከዊንክስ ዝውውር እስከ 40 ሚሊየን ዩሮ የሚቀርብለት ከሆነ ተጫዋቹን ለመሸጥ ዝግጁ እንደሆነ ተዘግቧል

 

ማን ሲቲ ለካሊዱ ኩሉባሊ የ 57 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ለናፖሊ አቅርቧል፥ሲቲዎች በመጨረሻው ስምምነት ላይ ቦነስ ክፍያ ለመክፈል እንደተዘጋጁ ቢነሳም ናፖሊዎች ለልጁ 63 ሚሊየን እንደሚፈልጉ The Sun ዘግቧል

 

የባየር ሙኒኩ አማካይ ቲያጎ አልካንትራ በሊቨርፑል እንደሚፈለግ ሲነሳ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ በፒኤስጂ እና ማንችስተር ሲቲ እንደሚፈለግ Le10sport ዘግቧል።

 

ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም በዚህ ክረምt አርጀንቲናዊውን የጁቬንቱስ አጥቂ ፓውሎ ዲባላ ለማስፈረም ሌላ ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚችል The Mirror ዘግቧል ፡፡

 

የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ኦዲዮን ኢጋሎ በፓሪስ ሴንት ዥርሜን የዝውውር ራዳር ውስጥ መግባቱን የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያ ግንኙነት መጀመሩም Foot Mercato ዘግቧል።

 

የማንቸስተር ሲቲው ዴቪድ ሲልቫ ከላዚዮ ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰ እና ፊርማውንም ሊያኖር እንደሆነ Corriere dello Sport ዝግቧል

 

የቀድሞው የቶትንሀም ተከላካይ ጃን ቬርቶንገን ቤኒፊካን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራ ለማድረግ መዘጋጀቱን BBC Sport ዘግቧል

 

ወልቭሶች አሰልጣኛቸውን ኑኖ ኢስፕሪቶ ሳንቶስን ለማቆየት በአመት 5ሚልየን ዩሮ የሚያገኝበትን ውል አቅርበውለታል።

 

 

ፍሬው ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.