ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

የዕርስ በርስ ግንኙነት

⚽️ ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል እስከዛሬ በሁሉም ውድሮች 197 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ 56 ጊዜ አርሰናል 96 ጊዜ ሲያሸንፉ 45 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል

⚽️ ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል ጋር ያደረጋቸውን የመጨረሻዎቹን ስድስት የፕሪምየር ሊግ እና የካፕ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፉዋል፡፡

⚽️ አርሰናል ከአንድ ቡድን ጋር ባደረገው ተከታታይ አምስት የሊግ ጨዋታዎች በሙሉ ሲሸነፍ እ.ኤ.አ 1977 ወዲህ የመጀመሪያው ነው( እ.ኤ.አ 1974 እስከ 1977 በተከታታይ 7 የሊጉ ጨዋታዎች ላይ በ ኢፕሲዊች ተሸንፈው ነበር)

⚽️ አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ ማንቸስተር ሲቲ ያሸነፈው እ.ኤ.አ. በ2017 በኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ነበር

 

ማንቸስተር ሲቲ

⚽️ በማንቸስተር ሲቲ በኩል ኤሚሪክ ላፖርት ከጉዳቱ አገግሞ ለጨዋታው የደረሰ ሲሆን በተመሳሳይ ነሀሴ ወር ጀምሮ ጉዳት ላይ የነበረው ሌሮይ ሳኔ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደጨዋታ ይመለሳል ፡፡

⚽️ ማንቸስተር ሲቲ በሊጉ ላይ ባደረጓቸው የመጨረሻ ዘጠኝ ግጥሚያዎች ኳስን ከመረብ ማዋሀድ ተስኑዋቸዋል

⚽️ ማንቸስተር ሲቲ በዘንድሮ የውድድር ዘመን 7 ጨዋታዎች ላይ ሽንፈቶችን ያስተናገደ ሲሆን ይህም ካለፉት 2 የውድድር ዘመናት ከገጠመው ሽንፈት በ 1 ይጨምራል

⚽️ ሰርጂዮ አጉዌሮ በአርሰናል ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻ 12 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን አስቆጥሯል

⚽️ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከአርሰናል ጋር ባደረጋቸው 7 የሜዳው ጨዋታዎች አልተረታም (W6 ፣ D1)

⚽️ ኬቨን ደ ቡሩየን አርሰናል ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ሰባት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች አራት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ሁለት ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል

⚽️ ማንቸስተር ሲቲ የዛሬውን ጨዋታ ተሸንፎ ሊቨርፑል ቀጣይ ጨዋታ ካሸነፈ፤ ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን ያረጋግጣል

 

 

አርሰናል

⚽️ የአርሰናል በኩል አሰልጣኙ ሚካኤል አርቴታ ምንም አይነት አዲስ ጉዳት በቡድኑ ውስጥ እንደሌለ የተናገረ ሲሆን ፤ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቀው የቆዩት ሉካስ ቶሬራ እና ካሉም ቻምበርስ ግን ከፊትነስ ጋር በተያያዘ በጨዋታው መሰለፋቸው አጠራጣሪ ሆኑዋል፡፡

⚽️ አርሰናል እ.ኤ.አ. 2020 የቀን መቁጠርያ አመት ከገባ ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ ሽንፈት አላስተናገዱም (W4, D4)

⚽️ አርሰናል በዘንድሮ የውድድር ዘመን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከሚበልጧቸው ክለቦች ጋር ባደረጋቸው የ11 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ አጋጣሚ ብቻ ነው (D5, L5)

⚽️ ፒየር-ኤሜሪክ ኦቦሚያንግ በ 75 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 49 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል – በዛሬው ጨዋታ ላይ ጎል ካስቆጠረ በውድድሩ 50 ጎሎ በጥቂት ጨዋታ ላይ ለመድረስ ስድስተኛው ፈጣን ተጫዋች ይሆናል ፡፡

⚽️ አሌክሳንድር ላካዜቴ በፕሪሚየር ሊጉ በተሰለፈባቸው የመጨረሻ 13 ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎች ኳስና መረብን ማገናኘት ተስኖታል

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.