መርሲሳይድ ደርቢ የሚካሄድበት ስታዲየም ተረጋገጠ!

ሰኔ 14 ሊካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት የሊቨርፑል እና የኤቨርተን መርሲሳይድ ደርቢ ምን አልባት ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ሊመጡ ይችላሉ በሚል ወደ ገለልተኛ እስታዲየም ሊቀየር እንደሚችል ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም ዛሬ የሊቨርፑል ከተማ አስተዳደር ሸንጎ አማካሪ ቡድን ጨዋታው በጉዲሰን ፓርክ ይከናወን ወይስ ወደ ገለልተኛ ስታዲየም ይዘዋወር በሚለው ሃሳብ ላይ መክረው ውሳኔ ያስተላለፉ ሲሆን በዚህም መሰረት ይህ ደርቢ በኤቨርተኑ ጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተረጋግጧል።

ማንቸስተር ሲቲ በአርሰናል ከተሸነፈና ሊቨርፑል በደርቢው ጨዋታ ድል ከቀናው ከ30 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን ማንሳቱን ያረጋግጣል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.