የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች 5 ቅያሪ እንዲያረጉ ተፈቀደላቸው!
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተወያይተው አዲስ ህግ ካፀደቁ በሁላ በየጨዋታው ከሶስት ይልቅ አምስት ተጫዋቾችን እንዲቀይሩ ተወስኗል ይህም የሆነበት ምክንያት የተጫዋቾቹን ደህንነት ለመጠበቅ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ነገሮች ላይ ተስማምተው የወሰኑ ሲሆን እነዚህም:
- ቡድኖቹ የቅያሬ ስም ዝርዝር ሲያወጡ ከተለመደው ሰባት ተጫዋቾች ይልቅ ዘጠኝ ተተኪዎችን መሰየም ይችላሉ
- አስፈላጊ ከሆነ ገለልተኛ ሜዳዎችን ለመጠቀም በመርህ ደረጃ ተስማምተዋል
- በእያንዳንዱ ጨዋታ በስታዲየሙ መገኘት የሚችለው አጠቃላይ የሰው ቁጥር ከ300 ማለፍ አይችልም
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሶስት ወር በኋላ በመጪው ሰኔ 10 እንደሚጀመር ይታወቃል