የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንዲጫወቱ ተፈቀደላቸው!

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ ከመጀመሩ በፊት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ለአወዳዳሪው አካል ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን ይህም ጥያቄያቸው በአወዳዳሪው አካል ተቀባይነትን አግኝቶ ፍቃድ እንደተሰጠው BBC ዘግቧል።

እነዚህ የወዳጅነት ጨዋታዎች ግን በጥብቅ መመሪያዎች እንደሚካሄዱ የተገለጸ ሲሆን እነዚህም መመሪያዎች:

  • ክለቦቹ ከዘጠና ደቂቃ ጉዞ በላይ ተጉዘው መጫወት አይችሉም፥ ምን አልባት እንደ ኒውካስትል ያሉ ክለቦች ተጨማሪ ደቂቃ መጓዝ ካለባቸው ልዩ ፍቃድ ይሰጣቸዋል
  • ሁሉም ተጫዋቾች ወደ ስታዲየም የሚሄዱት በራሳቸው መኪና ነው
  • ምንም አይነት ኦፊሻል ዳኛ አይመደብላቸውም
  • ከጨዋታው በፊት ስቴድየሙ/ የስልጠና ቦታው ግምገማዎች ይደረጉበታል
  • ከጨዋታው በፊት ተጫዋቾች መመርመር ይኖርባቸዋል

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.