አሜሪካዊው ቦክሰኛ የጆርጅ ፍሎይድን የቀብር ስነስርአት ወጪ ሊሸፍን ነው!

የ46 አምቱ የአምስት ጊዜ የአለም ቦክስ ሻምፒዮናው ፍሎይድ ሜይዌይዘር ከቀናት በፊት በፖሊሶች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱን ያጣውን ጆርጅ ፍሎይድ የቀብር ስነስርአት ሙሉ ወጪውን ሊሸፍን እንደሆነ ዛሬ ዘ ጋርዲያን ይዞ በወጣው ዘገባ ተገልጿል። የቦክሰኛው የማስታወቂያ ድርጅት የሆነው ሜይዌይዘር ፕሮዳክሽንም ይህ ዜና እውነት መሆኑን በትዊተር ገጹ ያሰፈረ ሲሆን የሟች ቤተሰቦችም መቀበላቸው ተያይዞ ተነስቷል።

የጆርጅ ፍሎይድ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተወለደበት ሂውስተን ከተማ ሰኔ 2 ቀን ይካሄዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.