ኒኮ ኮቫች ከባየር ሙኒክ ተሰናበተ
የጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየር ሙኒክ ከ18 ወራት በኋላ አሰልጣኙ ኒኮ ኮቫችን ከኃላፊነት አንስቷል፡፡ በመግለጫው እንደተጠቀሰው ውሳኔው በጋራ ስምምነት መደረጉን ገልጸዋል ፡፡ረዳት አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊች ረቡዕ በሻምፒዮንስ ሊጉ ኦሎምፒያኮስን እንዲሁም እሁድ በሊጉ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚገጥመውን ቡድን ይመራሉ፡፡
በቅዳሜው ጨዋታ በኢንትራክት ፍራንክፈርት 5-1 የተሸነፈው የአምናው ሻምፒዮን ሙኒክ በቡንደስሊጋ ደረጃ ሰንጠረዡ 4ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡