የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ
ሊቨርፑል ከ ቶትንሀም ሆትስፐርስ
አንፊልድ
እሁድ 16/02/2012 ምሽት 1፡30
ቶትንሀም ሆትስፐር ለመጨረሻ ጊዜ ከሊቨርፑል በሻምፒዮንስ ሊግ ከተጫወቱ በኋላ በቶትንሀም ቤት ብዙ ነገር በመልካም እየሄደ አይገኝም፡፡ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሁለቱ ቡድኖች በተቃራኒ አቅጣጫ እየሄዱ ይመስላል ፡፡ ቶተንሀም በሊጉ ውስጥ በእድሜ መግፋትና የተጫዋቾች በዝውውር ጉዳይ አለመረጋጋት እና ተያያዥ ችግሮች ክለቡ በተረጋጋ እና ወጥ በሆነ መንገድ መጓዝ ተስኖታል፡፡ ሊቨርፑል በተቃራኒው በሊጉ ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሲሆን ማግኘት ከሚገባው 27 ነጥብ 25 ነጥቦችን ወስደዋል ፡፡ይህም አስደናቂ የማጥቃት ብቃት፣ ጠንካራ ተከላካይ እና የቡድን መንፈስ ለያዘው ሊቨርፑል ቅድሚያ የማሸነፍ ግምት ወስዷል፡፡
በሊቨርፑል በኩል ረቡዕ ምሽት ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ያመለጣቸው ሁለቱ የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ለእሁዱ ጨዋታ የመድረስ እድላቸው የሰፋ ሲሆን በተለይ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ትሬንት አሌክሳንድር አርኖልድ ለጨዋታ ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ነገር ግን ክለቡ የጁኤል ማቲፕ የአካል ብቃት ደረጃው መረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡
ቶትንሀም ባለፈው ቅዳሜ በፕሪሚየር ሊጉ ግርጌ ከሚገኘው ዋትፎርድ ጋር 1 ለ 1 ከተለያየ በኋላ አሰልጣኙ በቡድኑ ላይ በርካታ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው በሳምንቱ አጋማሽ በሻምፒዮንስ ሊጉ ባደረጉት ጨዋታ 4 ተጫዋቾችን ቀይሮ የተጠቀመ ሲሆን በዚህም ጨዋታም የተወሰነ ለውጥ የሚኖር ይመስላል፡፡
በመጠነኛ ጉዳት ምክንያት የተወሰኑ ጨዋታዎች ያለፉት ክሪስቲያን ኤሪክሰን በአሰልጣኙ ከታመነበት ለጨዋታው ዝግጁ ነው፡፡ ከ 2019 መገባደጃ በፊት ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ከተረጋገጠው የክለቡ ካፒቴን ሁጎ ሎሪስ እና በክረምቱ ቡድኑን የተቀላቀለው ራያን ሴሴንዮን ውጪ ቡድኑ አዲስ የጉዳት ዜና በቶትንም በኩል የለም፡፡
⚽️ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አሰላለፍ
ቶትንሀም ሆትስፐር፡- ጋዛኒጋ፣ ኦሪዬ፣ ቬርቶገን፣ ሳንቼዝ፣ ዴቪስ፣ ሲሶኮ፣ ንዶምቤሌ፣ ዴሊ አሊ፣ ላሜላ፣ ሰን፣ ኬን
ሊቨርፑል፡- አድሪያን፣ አ. አርሎንድ፣ ቫንዳይክ፣ ማቲፕ፣ ሮበርትሰን፣ ሄንደርሰን፣ ፋቢኒሆ፣ ኬዬታ፣ ማኔ፣ ፈርሚኖ፣ ሳላህ