“ማንም ሰው ከእንግዲህ ኦልድ ትራፎርድን አይፈራም ”
“እኛ ከእነሱን ጋር በኦልድትራፎርድ እንጫወታለን፣ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተናል ፣ አድናቂዎቻቸው ቡድናቸው እንደሚያሸንፍ ይጠብቃሉ ፣ ተጫዋቾቹ አሸናፊ እንደሚሆኑ ይጠብቃሉ…”
“… ኦ! ያ አስፈሪ መንፈስ አሁን ሄዷል ሰግቼላቸዋለሁ፡፡”
“ጠፍቷል ፣ ተገፏል ( እርቃን ቀርተዋል)፤ እናም ተመልሶ ለመመለስ ዓመታት ይወስዳል።”
“የተለያየ መንገድ በማድረግ መልሰው ማግኘት ይችላሉ፣ የተወሰኑ ጥቂት ግለሰቦች ፣ አሸናፊዎች ፣ እዚያ ቦታ ለመድረስ በምንም የማይቆሙ ሰዎች አሉ ፡፡”
“ግን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ የጎደለው ነገር ይህ ነው ፡፡ ከእንግዲህ ፍርሃት የለም።”
“አሁን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ስትሄድ …… ሮችዴልም ጭምር ወደ ኦልድትራፎርድ ከሄደ ውጤትን ለማግኘት አስቦ ነው፣ በቅርቡ በፕሪምየር ሊግ 6 ጎሎችን አስተናግደው በሜዳቸው መሸነፋቸው ይታወሳል፤ ስለዚህ ማንኛውም ቡድን እዚያ በመሄድ ውጤት ማግኘት እንደሚችል አምኗል፡፡”
“ወደእዚያ ቀን ልመልሳችሁ፣ ሰዎች(ደጋፊዎች) ከአንደኛው ደቂቃ ፣ ከሁለተኛው ደቂቃ ጀምሮ ኳሱን መረብ ውስጥ እየጠበቁ ነበር ፡፡ እኛ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እግርበእግር እየተጓዝን ነበር ወደዚያ በሄድንበት ጊዜ ምንም ፍርሃት አልነበረንም ፣ ነገር ግን በዚያ በገጠመን ድባብ ምክንያት እኛን ጨምሮ ሌሎቹም የቡድን አባላት ተጨንቀን ነበር ፣ ግን ያ አሁን የለም ጠፍቷል፡፡”
“አስፈሪው ድባብ አሁን ወደ ሊቨርፑል ተመልሷል ፣ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ተመልሷል ፣ እናም አሁን ማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ሥራ ይጠበቅበታል ፡፡”
ይህን ያለው በ2003 በኦልድትራፎርድ ሜዳ ላይ ቫንኒስተሮይ ጋር ግብግብ ውስጥ ገብቶ የነበረው “የቀድሞውን የመድፈኞቹ ተከላካይ ማርቲን ኬዌን“ ነው፡፡
ሌሎች የእግር ኳስ ባለሙያዎችም በኬዌል ሐሳብ ላይ ይስማማሉ፡፡ ለምሳሌ የቀድሞው ክሪስታል ፓላስ ሊቀመንበር ሲሞን ጆርጅ ስንወስድ የኦልድትራፎርድ ግርማ ሞገስ ከቀድሞ የክለቡ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጡረታ መውጣት በኋላ ሞቷል ወይም አክትሞለታል በማለት በሐሳቡ ይስማማሉ፡፡ አክለውም በአሁኑ አሰልጣኝ ኦሌጎናር ሶልሻየር አስፈሪነቱን መልሰው ያገኛል ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል፡፡
“ግን..” ይላሉ ሲሞን “ግን ደግሞ፣ ያ የማንቺስተር ዩናይትድ መልክ እና የእግር ኳስ እንቅስቃሴ (ሰር አሌክስ) ፈርጉሰን እንደነበሩበት ጊዜ ይሆናል፡፡በእውነት ግን ማንቸስተር ዩናይትድ የሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲን ያሉበት ሀያል ሚዛን ላይ ወይም ወሳኝ ጊዜ ጋር ይስተካከላል? የኦሊጎናር ሶልሻየር የያዘው መንገድ ግን እዚያ ደረጃ ያደርሳቸዋል? አይመስለኝም! ”
የማንቸስተር ሲቲውም አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስለዚህ ጉዳይ በአንድ አጋጣሚ ተጠይቀው አስፈሪው ድባብ ከራቃቸው እንደቆየ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
እንደተናገሩት “ለመሄድ/ለመጫወት ቀላል ቦታ አይደለም፣ ነገር ግን ለመጫወት የሚያስፈራ ምንም ምክንያት የለም፡፡ እኛ ማድረግ ያለብንን በትክክል እናውቃለን ፡፡”
“ጥሩነቱ ክለቡ በጥሩ ሁኔታ የተዋቀረ መሆኑ አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን በዩናይትድ ውስጥ ምን እንደተከሰት አስተያየት መስጠት አልፈልግም ፡፡ በአለፉት ዓመታት ውስጥ ይህ ክለብ በጣም አድጎ ነበር ፣ አሁን ላይ ግን ወደ ኦልድትራፎርድ ለመሄድ ምንም አያስፈራም እኛ በተሻለ አቅም መጫወት እንችላለን፡፡”
“ነገ ምርጥ ዩናይትድ እጠብቃለሁ ፣ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ በክለባቸው ኩሩ ናቸው ፡፡ ጨዋታቸው ላይ እንደ ሁልጊዜያቸው ጠንክረው ከሰሩ ጨዋታዎቻቸውን ለማሸነፍ ይችላሉ” ብሏል፡፡”
የቀድሞ የሊቨርፑልና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ስታን ኮሊሞር በበኩሉ የማንቺስተር ዩናይትድን ሞገስ ማጣት በሰፊው አብራርቷል፡፡ ኮሊሞር ሲጀምር “ ኦልድትራፎርድ የአስፈሪነት ግርማውን አጥቷል” ይላል፡፡
“ማንቺስተር ዩናይትድ በቀድሞ ታሪኩ ብቻ እየኖረ ያለ ይመስለኛል ሌላው ቢቀር ስታዲየሙ እንኳን አስደናቂ ገፅታውን አጥቷል፡፡”
“እኔ ከተጫወትኩባቸው ስታዲየሞች ከዌንብሌይ ጋር ብቸኛው ስታዲየም ነበር መጀመሪያ ወደሜዳ እንደወጣው ኦ! እዚህ ያገኘሁትን ሁሉንም የኔ በሆኑ የሚያሰኝህ፣ ምክንያቱም እንደገና እዚህ መመለስህን እርግጠኛ አትሆንም ፡፡
“አንጋፋው ሜዳ ሌላ ምስጢር አለው ሌሎቹ የሌላቸው እና ለማንኛውም ተጫዋች ወደ እዚያ ለመሄድ የሚያስደስት ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡”
“ችግሩ ፣ ያ ረቂቅ ነገር በጨዋታ ላይ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ባለበት ሁኔታ ምስጢራዊነቱ በፍጥነት ሊጠፋ ይችላል ፣ በእርግጥም ማንቸስተር ሲቲ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዚህ ሜዳ እያገኛቸው ያለው ድሎች እንደሚያመለክቱት በኦልድትራፎርድ ያ ድባብ እንደሌለ ያሳያል፡፡”
“እኔ የዩናይትድ ደጋፊ ብሆን ብዙ ነገር ያስጨንቀኛል ፣ ምክንያቱም አሁን ለሰባት ዓመታት የእንግሊዝ ሻምፒዮናዎች ስላልሆኑ እና ከሲቲ እና ከሊቨር ጀርባ የሚሆኑባቸው ወቅቶች ሁለት ሶስት እያሉ ነው ፡፡”
“ሲቲ እና ቼልሲ ገና በታዳጊ እና በሴቶች እግር ኳስ ውስጥ ሁሉንም እያሸነፉ ነው ፣ እናም ዩናይትድ በእውነቱ አሁንም በአገሪቱ ትልቁ ክበብ ከሆነ ታዲያ በወጣቶች እና በሴቶች እግር ኳስ ግንባር ቀደም ክበብ መሆን አለባቸው።”
“ዩናይትድ ወጣት ተጫዋቾችን በማምጣት አስደናቂ ባህል ነበረው ሁልጊዜ ግን እንደ ቤካም፣ ስኮልስ እና ኒኪ ባት ምን ያህል ልጆችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳድገዋል?”
“ኤድ ዉድዋርድ ዩናይትድ የእግር ኳስ ዳይሬክተርን ወይም በሌላ ማዕረግ ትክክለኛውን ሰው መቅጠር እንዳለባቸው ሳይገነዘቡ የቀሩ አይመስለኝም” ይላል
“በአነስተኛ በጀት ላይ ተፈላጊውን ብቃት ያላቸው እና ያንን አይነት ሚና በጥሩ ሁኔታ እየሠሩ ያሉ ብዙ ጠንካራ እጩዎች አሉ ፡፡ ሞናኮ ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሴቪላ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሀብታቸውን እጅግ በጣም የተሻለ መልኩ እንዲጠቀሙ ያረጉ ሰዎች አሏቸው ለምን ወደዚያ አይሄዱም?”
“ዩናይትድ የሚቀጥሉትን ጊዜያት ውድ ሀብት መሆን የሚችሉትን እንደ ኔቢ ኬይታ ወይም ኑጎሎ ካንቴን አይነቶቹን የሚመለከቱ ሰዎችን ማግኘት አለበት ምክንያቱም እንደዚያ ለማድረግ ሀብቶች አሏቸው፡፡”

“ለበርካታ ዓመታት አሁን ዩናይትድ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ከፊት ቀድመው ከመሄድ ይልቅ ከባዱን መንገድ ሲከተሉ ቆይተዋል፡፡”
“እናም እንደ ቀድሞ የእንግሊዝ ታላቅ ክበብ ሆነው ወደቆዩበት ጊዜ ቦታ መመለስ ከፈለጉ በፍጥነት መደርደር አለባቸው፡፡” ሲል አስተያየቱን አጠናቋል፡፡
ከእግር ኳስ ባለሙያዎቹ በተጨማሪም ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ከሆነም በእውነትም ኦልድ ትራፎርድ ረቂቅ ሚስጥሩን አጥቷል፡፡ በተጋጣሚዎች በጨዋታ መበለጥ፣ ጎሎችን ማስተናገድ ብሎም ሽንፈት ዩናይትድ በዚህ ሜዳ ላይ እየለመደው የመጣ ይመስላል፡፡
ሁሉም እንደሚስማሙበት እና ሁኔታዎች እንደሚያሳዩትም ከሆነ ዩናይትድ እና ግሌዘሮች በጊዜ የማይነቁ ከሆነ እንደሊቨርፑል፣ በኤሲ ሚላን እና ማርሴይ ሁሉ የቅርብ ጊዜያት የታላቅነቱ ዘመናት ቀን የመሸባቸው ይመስላል፡፡
