ኢትዮ ቴሌኮም ለሚዲያ ተቋማትና ተጠቃሚዎች ታላቅ የምስራች ይፋ አደረገ!

የሀገራችንን የሚዲያ ስነ-ምህዳር በእጅጉ የሚቀይር “ቴሌስትሪም” የተሰኘ በኢንተርኔት የሚሰራ በአይነቱ ለየት ያለ የይዘት ስትሪሚንግ አገልግሎት መጀመሩ በይፋ ተዋውቋል።

በተጨማሪም የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት አሰጣጥን ሙሉ በሙሉ የሚያዘምን የፊክስድ ብሮድባንድ (ዋይ ፋይ) አገልግሎት “ንክኪ-አልባ ዲጂታል አሰራር” በተመለከተ የካቲት 13/2018 ዓ.ም በዋና አስፈጻሚው ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በኩል ይፋ ተድርጓል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ እያንዳንዱን አሰራር እና ያለውን ጠቀሜታ በምስል በማስደገፍ በሰፊው ያብራሩ ሲሆን ይህም ማብራሪያ በእለቱ ከነበሩ ተመዳሚዎችን እና እንግዶችን ያስደመመ እና ያስደሰተ በመሆኑን ታዳሚዎቹ በመጨረሻ በሰጡት አስተያየት እና ጥያቄዎቻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

በየጊዜው አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ የሚያደርገው ኢትዮ ቴሌኮም በእለቱ ታዋቂ አርቲስቶች የሚዲያ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ፣ እና የሚዲያ ባለቤቶች ፣እንዲሁም ጋዜጠኞች እና ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይፋ የሆነው አገልግሎት ስማርት ያልሆኑ ቴሌቪዥኖችን ወደ ስማርትነት በመቀየር ዘመናዊ የስትሪሚንግ አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ፈር ቀዳጅ አገልግሎት መሆኑን ተነግሯል።

በእለቱ በዋና ስራ አስፈጻሚዋ በኩል እንደተገለጸው በአሁኑ ወቅት ከ60 በላይ የቀጥታ ስርጭት ቻናሎችን እና ከ350 በላይ በፍላጎት የሚታዩ ቪዲዮዎችን የያዘው የቴሌስትሪም አገልግሎት፤ በመደበኛ ብሮድባንድ፣ በሲም ካርድ እንዲሁም የ‘Set Top Box’ (STB) መሣሪያን በመጠቀም የስትሪሚንግ አገልግሎት ከማቅረብ ባሻገር፣ ስማርት ያልሆኑ ቴሌቪዥኖችን ወደ ስማርትነት በመቀየር ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል።
ይህም ዘመናዊ የዲጂታል መዝናኛን ለእያንዳንዱ ቤት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ቴሌስትሪም ለሀገራችን የሚዲያና የመዝናኛ ስነ-ምህዳር ተዋንያን አዲስ የዕድገት አድማስ የከፈተ ሲሆን፤ በዚህም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የፕሮዳክሽን ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች፣ የፊልም አዘጋጆችና ተዋንያን እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና እና በማህበረሰብ እሴት ግንባታ ላይ የሚሰሩ አካላት የሀገራችንን ብሄራዊ እሴት የጠበቁ ይዘቶቻቸውን በስፋት ተደራሽ የሚያደርጉበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሰፊ ስትራቴጂያዊ ዕድል እንደሚፈጥር የተነገረ ሲሆን ይህም በእለቱ ከነበሩ ታዳሚዎች ከፍተኛ ምስጋና አድናቆት ተችሮታል።

ይህ ፕላትፎርም የሀገራችንን ባህል፣ እሴትና ስነ-ምግባር መሰረት ያደረጉ ይዘቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፤ የወላጆች ቁጥጥር ሥርዓት መካተቱ አስተማማኝና ተመራጭ ያደርገዋል።

ቴሌስትሪም የሚዲያ ተቋማት ለሳተላይት ኪራይ የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር ሲሆን፤ ለፊልም ፕሮዲውሰሮች፣ ይዘት ፈጣሪዎች፣ ለትምህርት እና ለቢዝነስ ተቋማት አማራጭ ይፈጥራል፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው ኢትዮ ቴሌኮም የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት በማዘመን “ንክኪ-አልባ” የደንበኞቻችንን ተሞክሮ በእጅጉ የሚያሻሽል የዲጂታል ሲስተም ተግባራዊ ማድረጉን ተገልጿል።

ይህም ደንበኞች ካሉበት ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒ-መተግበሪያ አዲስ ዋይፋይ እንዲጠይቁ ወይም የብልሽት ምዝገባ እንዲያከናውኑ ያስችላል ተብሏል ፡፡

ደንበኞቻችን የቴሌስትሪም አገልግሎትን በዘመን ገበያ ወይም በአገልግሎት ማዕከሎቻችን፤ የብሮድባንድ አገልግሎታችንን ለማግኘት በቴሌብር ሱፐርአፕ እና በአቅራቢያዎ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ እንዲጠቀሙ በሰፊው ማብራሪያ ላይ ተገልጿል፡፡

በእለቱ ከኢተዮ ቴሌኮም በዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት አለሙ እና በኩባንያው ባለሙያዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከተሰጠ በዃላ
ጥሪ ከተደረገላቸው እንግደችና፣ታዋቂ አርቲስቶች ፣የሚዲያ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ፣ እና የሚዲያ ባለቤቶች ፣ እንዲሁም ከጋዜጠኞች የተለያዩ በርካታ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን ለዚህም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወይዘሪት ፍሬ ህይወት አለሙ ለያንዳንዱ ጥያቄ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

✍️ፈለቀ ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.