ፕሪስትያኒ ቪንሽየስን ምን እንዳለው ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተናገረ!

የዘረኝነት ስድብ ተሳድቧል በሚል የተጠረጠረው የቤኔፊካው ተጫዋች ጂያንሉካ ፕሪስትያኒ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ምርመራ መጀመሩን ተከትሎ ቃሉን የሰጠ ሲሆን ቪንሽየስን የሰደብኩት ስድብ ” ግብረሰ*ማዊ” እንጂ የዘረኝነት ስድብ አይደለም ሲል ራሱን ተከላክሏል። ከሁለቱም ጋር የተያያዙ ስድቦችን መሳደብ ግን በህጉ መሰረት ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚያስከትል የተለያዩ ዘገባዎች አስረድተዋል።

በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ህግ መሰረት ግብረ ሰ*ማዊነትን ማጥላላትም( Homophobic) ሆነ የዘረኝነት( Racism) ስድብ መሳደብ ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚያስከትል የተቀመጠው አንቀፅ ያሳያል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የዲሲፕሊን ህግጋት አንቀፅ 14 ላይ እንደተቀመጠው ከሆነ አንድ ሰው በቆዳ ቀለም፣ ዘር፣ የትውልድ ቦታ፣ የፆታ ሁኔታ፣ ሀይማኖት ላይ ተመርኩዞ አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን ከሰደበ 10 ወይም ከዛ በታች ጨዋታዎች የሚደርስ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል። ከጨዋታ ቅጣት በተጨማሪም ሌሎች እንደአስፈላጊነቱ ትክክለኛ ናቸው ተብለው የታመኑ ቅጣቶች ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንቀፁ ያትታል።

ይህን ተከትሎም ጂያንሉካ ፕሪስትያኒ ከቅጣት የመዳኑ ነገር ጠባብ እንደሆነና ምርመራው ሲጠናቀቅ ቅጣቱ እንደሚጣልበት ዘገባዎች አያይዘው ገልፀዋል።

ESPN

Leave a Reply

Your email address will not be published.