አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጌታነህ ከበደ ውሳኔ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጌታነህ ከበደ ውሳኔ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ
ብሄራዊ ቡድኑን አስመልክቶ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የነበረው ጌታነህ ከበደ ራሱን ማግለሉን አስመልክቶ ለቀረበላቸው
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መል ሰጥተዋል ።
👉ጌታነህ ራሱን ያገለለው በርስዎ ውሳኔ ወይስ በራሱ ፍላጎት ነው በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ👉
ለ28 ተጫዋቾች በተደረገው ጥሪ ተጫዋቾች ታህሳስ 18 ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ከቀረበ በዃላ ጌታነህ ከበደ ቡድኑን የተቀላቀለው ዘግይቶ በትናንትናው ዕለት ነበር ሆኖም ሆቴል መግባቱን እና ጂምናዚየም መስራቱ እዳልነገራቸው እና መረጃው እንዳልነበራቸው
መምጣቱን ካወቁ በኋላም ከቀሪው የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ጋር ተጫዋቹን በማስቀመጥ ምክንያቱን ቢጠይቁትም ጥሪውን ባለመስማቱ እንደዘገየ ምላሽ እንደሰጣቸው እና ይህም አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሰው
ከዚህ ቀደም ከቤተሰብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፍቃድ ጠይቀው የነበሩት አማኑኤል ገብረሚካኤል እና አስቻለው ታመነ የመሰሉ ተጫዋቾችን ከስብስባቸው ውጪ አቆይተው በሌላ ጥሪ መልሰው እንዳካተቷቸውም አስታውሰዋል።
በመሆኑም ለጌታነህም ከቀሪው ስብስብ የተለየ አሰራር ስለማይኖር በስብስቡ ውስጥ ማስቀጠል እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በአሰልጣኙ እና በተጫዋቹ መካከል የነበረው አለመግባባት ከመሰለፍ እና አለመሰለፍ ጋር ብቻ የሚገናኝ እና ቀደም ብሎ ሙሉ ለሙሉ በውይይት የተፈታ መሆኑን እንዲሁም ትናንት ከተፈጠረው ጋር የሚገናኝ አለመሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ይህ መግለጫ ከመሠጠቱ አንድ ቀን በፊት ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሄራዊ በድን ማግለሉን ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ መግለጹ ይታወቃል።

