መድፈኞቹ ነጥብ ጥለዋል።

መድፈኞቹ ነጥብ ጥለዋል

በአስራ ሶስተኛዉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መሪዎቹ አርሰናሎች ከ ሳውዝአምፕተን ጋር ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።

በጨዋታው ግራኔት ዣካ በ11′ ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ክለቡን መሪ ቢያደርግም በ65’ኛው ደቂቃ ላይ አርምስትሮግ አስቆጥሮ ሳውዝ አምፕተን ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችሎታል ።

አርሰናል በ28 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሳውዝአምፕተን ደግሞ በ12 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ኖቲንግሀም ፎረስት እሁድ ጥቅምት 20 በ11 ሰአት እንዲሁም ሳውዝሀምፕተን ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ቅዳሜ ጥቅምት 19 በ11 ሰአት የሚጫወቱ ይሆናል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች

አስቶንቪላ 4-0 ብሬንትፎርድ

ሊድስ ዩናይትድ 2-3 ፉልሃም

ወልቩስ 0-4 ሌስተር ሲቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.