ባህርዳር ከድሬዳዋ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
በ4ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ውሎ 10:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸዉን ያካሄዱት ባህርዳር ከተማና ድሬዳዋ ከተማ አንድ ለአንድ በሆነ የአቻ ዉጤት ጨዋታቸዉን አጠናቀዋል።
በጨዋታዉ የመጀመሪያ አጋማሽ 28ኛ ደቂቃ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ያሬድ ታደሰ ወደ ግብ በመቀየር ድሬዳዋ ከተማን መሪ ማድረግ ችሎ የነበረ ሲሆን ከእረፍት መልስ 60ኛው ደቂቃ የድሬዳዋው እንየው ካሳሁን ዱሬሳ ሹቢሳ ላይ ጥፋት በመስራቱ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱን ተከትሎ
ሙሉ ለሙሉ ጫና በማድረግ የተጫወቱት ባህርዳሮች በ77ኛዉ ደቂቃ ዱሬሳ ሹቢሳ የአቻነት ኳስ ከመረብ አሳርፏል። ጨዋታዉም በዚሁ የአቻ ዉጤት ተጠናቋል።
በአምስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኞ ጥቅምት 14 7:00 ሰዓት በሚደረገዉ የመጀመሪያ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ የሚጫወት ሲሆን ባህር ዳር ከተማ ረቡዕ ጥቅምት 16 7:00 ሰዓት ላይ ከለገጣፎ ለገዳዲ ይጫወታል።
7 ሰአት በተከናወነ ጨዋታ አርባምንጭ ከሀዲያ ሆሳህና ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
