የኢትዮጵዊያን አንፀባራቂ ድል በሊዬቪን
▪️በፈረንሳይ ከተማ ሊዬቪን በተካሄደው የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አመርቂ ድል አስመዝግበዋል።
▪️በ1500 ሜትር ኖርዌያዊው የ21 አመቱ ኢንግብሪስተን 3:30:60 በመግባት በኢትዮጵያዊው ሳሙኤል ተፈራ ተይዞ የነበረውን የአለም ሪከርድ አሻሽሎ በአንደኝነት ውድድሩን አጠናቋል። ሳሙኤል ተፈራ 3:33:70 በመግባት 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ስፔናዊው አግናሲዮ ፎንቴስ 3:37:59 በመግባት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

▪️በ3000ሜትር ሴቶች ከ4 አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ማካሄድ የቻለችው ዳዊት ስዩም 8:23:24 በመግባት ቀዳሚ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች። የገባችበትም ሰአትም የምንጊዜም 4ኛው ፈጣን ሰአት ሆኖ ተመዝግቦላታል። እጅጋየሁ ታዬ 8:26:77 እንዲሁም ሌላዋ ኢትዮጵያዊ ፋንቱ ወርቁ 8:38:15 ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

▪️በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ ፣ ጌትነት ዋሌ እና ለሜቻ ግርማ ሁሉም የተካፈሉበት ይህ ውድድር የአለም ሪከርድ ይሻሻልበታል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይሆን ቀርቷል። አስደናቂ ፉክክር በማድረግ ግን የተመልካች ቀልብ የያዘ ውድድር ነበር። ለሜቻ ግርማ 7:30:54 በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ከ12 ማይክሮ ሰከንዶች በኋላ ሰለሞን ባረጋ 7:30:66 በመግባት 2ኛ ሆኗል። ጌትነት ዋሌ 7:30:88 ሶስተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።

▪️በሴቶች አንድ ማይል ውድድር አሁንም ኢትዮጵያዊያን የደመቁበት ውጤት ተመዝግቧል። ጉዳፍ ፀጋዬ 4:21:72 በመግባት 1ኛ ስትሆን አክሱማዊት አምባዬ 4:25:30 ሁለተኛ ሆናለች ሂሩት መሸሻ 4:27:19 በመግባት ሶሰተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።

ፈለቀ ደምሴ።
