በነገው ዕለት ማዳጋስካርን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል።

በነገው ዕለት ማዳጋስካርን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል።
በነገው ዕለት የምድቡ አምስተኛ ጨዋታውን ከማዳጋስካር ጋር ያደርጋል። ብሔራዊ ቡድኑም ጨዋታው በሚደረግበት ባህር ዳር ዝግጅቱን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ከቀናት በፊትም ከማላዊ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አከናውኖ 4-0 አሸንፎ እንደነበር ይታወቃል ።
ወሳኙን የምድብ ጨዋታ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የሚገኘው ቡድኑ ዛሬ ከጨዋታው በፊት ያለውን የመጨረሻ ልምምድ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አከናውኗል። በልምምዱም ቡድኑን ለነገው ጨዋታ የሚያዘጋጁ ቀለል ያሉ የቡድን መንፈስን ሚገነቡ እንቅስቃሴዎችን አድርጓል።የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ተጫዋቾቹ በሥነ-ልቦናው ረገድ ከተጋጣሚ ተሽለው እንዲገኙ የሚያስችሉ ምክሮችን ለቡድኑ ሰጥተዋል። ተጫዋቾቹንም የራሳቸውን አጨዋወት ብቻ ሜዳ ላይ እንዲተገብሩ እና በተጋጣሚ ቡድን የጨዋታ አቀራረብ እንዳይደናገጡ መክረዋል። ከቀናት በፊት ቡድኑን እንደ አዲስ የተቀላቀሉት ወንድሜነህ ደረጄ እና መሳይ ጳውሎስም ከቡድኑ ጋር ልምምድ እየሰሩ እንደሆነ ታውቋል።

ከነገው ጨዋታ በፊትም የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች የቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸውን ምሽት ላይ ለጋዜጠኞች እንደሚሰጡ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.