ማክሎይድ ዘይት እና ሉበርካንት ወደኢትዮጵያ ገበያ መግባቱን ያበሰረበት ዝግጅት ተካሄደ!

ማክሎይድ የተሰኘ መቀመጫውን በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ያደረገና ተደራሽነቱን በመላው አለም በማስፋፋት ላይ ያለ የዘይት እና ሉበርካንት ማምረቻ ተቋም ከአማጋ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ወደኢትዮጵያ ገበያ መግባቱን ያበሰበረበት ዝግጅት ዛሬ መስከረም 15/2017 አ.ም በኢንተር ሌግዥሪ ሆቴል ተካሄዷል።

በዝግጅቱ ላይ የማክሎይድ ዘይት እና ሉበርካንት ጀነራል ማናጀር የሆኑት አቶ አህመድ ሺጊዲ እና ሌሎች የተቋሙ ሰራተኞች ብሎም የአማጋ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጀነራል ማናጀር ዶ/ር በላይነህ እና የማርኬቲንግ ሀላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ሰራተኞችም ተገኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች በአውቶሞቲቭ ዙሪያ የሚሰሩ የሚዲያ አካላት፣ የመኪና ጥገና ማእከል ባለቤቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በስነ-ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል።

ማክሎይድ የመኪና ዘይትን በአስተማማኝነት በማቅረብ በኩል አሽከርካሪዎች ይገጥማቸዋል ተብሎ የሚታሰበውን ችግር እንደሚፈታም ተነግሮለታል።

የማክሎይድ ምርቶች ለእይታ ቀርቀበውም ገለፃ ተደርጎባቸዋል። በባለሙያዎችም ከተለያዩ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.