አርሰናል ድል ሲቀናው ማን ሲቲ ነጥብ ጣለ

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ አስቶንቪላ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ማን ሲቲ ከኖቲንግሀም ፎረስት ነጥብ ተጋርቷል ።

ለአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦቹን ማርቲኔሊ ፣ ቡካዩ ሳካ ፣ ዚንቼንኮ እና ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ አስቶን ቪላን ከሽንፈት ያልታደጉ   ግቦችን ደግሞ ኩቲንሆ እና ዋትኪንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ አራት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ አስቶንቪላ በበኩላቸው በሀያ ስምንት ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች ደግሞ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል ።

የማንችስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ በርናንዶ ሲልቫ ሲያስቆጥር የኖቲንግሀም ፎረስትን የአቻነት ግብ ደግሞ ክሪስ ዉድ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ አቻ መውጣቱን ተከትሎ ነጥቡን ሀምሳ ሁለት በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ አርሰናል በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ 2 ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላ የሊጉ መርሀ ግብር

   ብሬንትፎርድ 1-1 ክሪስታል ፓላስ
⚽️ጃኔልት               ⚽️ኤዜ
ብራይተን 0-1 ፉልሃም
⚽️ ሶሎሞን
ቼልሲ 0-1 ሳውዛፕተን
⚽️ዋርድ ፕራውስ 45+1
ኤቨርተን 1-0 ሊድስ
⚽️ኮልማን

ወልቭስ 0-1 በርንማውዝ
⚽️ታቬርነር

Leave a Reply

Your email address will not be published.