ለደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደረገ።
ለደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደረገ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሀገር በቀሉ Endo- Ethiopia Tour & Travel Operators እና ከስፔኑ Runners for Ethiopia ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ከህዳር 19-22/2015 ዓ.ም ድረስ የፊዚዮና የማሳጅቴራፒ ስልጠና ሲሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ከስፔን ሀገር ይዘው የመጡትን የስፖርት ትጥቅ ደግሞ የኢ.አ.ፌ የፋሲሊቲና ማህበራት፣ አትሌቶች አገልግሎት የስራ ሂደት የሆኑት አቶ አሠፋ በቀለ ከስፔን ልዑካን ጋር በመሆን ለደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ድጋፉን አድርገዋል።
እንደ አቶ አሠፋ ገለፃ ለተቀሩት የማሠልጠኛ ማዕከላት ደግሞ ፌዴሬሽኑ ከሚያደርገው አመታዊ የትጥቅ ድጋፍ ጋር በማከል ከስፔን ሀገር የመጣው ትጥቅ እንደሚደርሳቸው አሳውቀዋል። ፌዴሬሽኑ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን ያመሠግናል።
መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው
