9ኛው የ 30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተጠናቀቀ

9ኛው የ 30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር
ተጠናቀቀ

በሴቶች

1ኛ) አትሌት አፀደ ባይሳ ከኦሮሚያ ፖሊስ

2ኛ) ፍቅርተ ወረታ ከመቻል

3ኛ) ብዙአገር አደራ ከኢ/ን/ባ

4ኛ) ሙሉዬ ደቀቦ ከኦሮ/ፖሊስ

5ኛ) ብሪሆ አዳነ ከከኢት/ን/ባንክ

6ኛ) አይናዲስ ተሾመ ከኢት/ኤሌክትሪክ

7ኛ) ጠጂቱ ገቢሳ ከከኦሮ/ፖሊስ

8ኛ) ሰአዳ አወል ከ ደቡብ ክልል ከ1ኛ-8ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

👉 በወንዶች የ30 ኪ. ሜ ውድድር

1ኛ) ፋንታሁን ሁነኛው ከኢት/ንግ/ባንክ

2ኛ) መኳንንት አየነው ከኢት/ንግ/ባንክ

3ኛ) አብዱ አስፋው በግል

4ኛ) በላይ ጥላሁን ከኢት/ንግ/ባንክ

5ኛ) ልመንህ ጌታቸው ከመቻል

6ኛ) አሰፋ መንግስት በግል

7ኛ) ጎሳ አምበሉ በግል

8ኛ) ነጋሲ ቱጂ ከኢት/ንግ/ባንግ በመሆን አጠናቀዋል።

በመቀጠልም ለውድድሩ መሳካት የከተማ አስተዳደሩ ቢሮዎች የሰርተፊኬት እና የእውቅና ሽልማት ተካሂዷል። ለውድድሩ አሸናፊዎች የገንዘብ እና የዋንጫ ሽልማት ስነ-ስርዓት ተደርጓል። ሽልማቶቹን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሠፋ ፣ የኦ/ብ/ክ/መ/የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሳሚያ አብደላ ፣ የኢ.አ.ፌ ፕሬዝደንት ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የኢ.አ.ፌ ስራ አስፈፃሚዎች ወ/ሮ ሳራ ሀሰን እና ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ አበርክተዋል።

የዋንጫ ሽልማቱን በሴት ኦሮሚያ ፖሊስ የወሰደ ሲሆን በወንዶች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወስዷል።

ውድድሩ በጥሩ ሁኔታና በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዘግቧል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.