ባርሴሎና በግብ ተንበሽብሾ አሸናፊነቱን አስቀጥሏል

ባርሴሎና በግብ ተንበሽብሾ አሸናፊነቱን አስቀጥሏል
በ11ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ጨዋታ በባርሴሎናና በአትሌቲኮ ቢልባሆ መካከል የተደረገ ሲሆን ባርሴሎና 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ጎሎች ዴምቤሌ በ12ኛዉ ሮቤርቶ በ19ኛዉ ሌዋንዶውስኪ በ22ኛዉ  ቶሬስ በ73ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።

ባርሴሎና በ28 ነጥብ የሊጉ 2ኛ ደረጃ  ላይ ሲቀመጥ ከመሪዉ ሪያል ማድሪድ ያለዉን ልዩነት ወደ 3 አጥብቧል። በአንፃሩ አትሌቲኮ ቢልባሆ በ18 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በቀጣይ የሊጉ መርሀግብር ባርሴሎና ከቫሌንሽያ እንዲሁም  አትሌቲኮ ቢልባሆ ከቪላሪያል የሚጫወቱ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.