በኦስትሪያ በተካሄደዉ የኦበር ባንክ ሊንዝ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ ኬኒያውያኑን አስከትሎ አሸንፏል።
በኦስትሪያ በተካሄደዉ የኦበር ባንክ ሊንዝ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ 2:06:16 በሆነ ሰዓት ዉድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ አሸንፏል።
ኬንያዊዉ ቤትዌል ቹምባ 2:06:26 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሲሆን ሌላኛዉ ኬንያዊ አትሌት ዳግላስ ቼብሊ 2:06:31 በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሁኖ አጠናቋል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አየለ አብሽሮ 2:09:37 ሰዓት በማስመዝገብ 10ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።