ሀገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ቀብራቸው በፓሪስ ተፈጸመ
የስፖርት ጋዜጠኛች የማህበር መስራችና፣ በካፍ እና ፊፋ ውስጥ ለረጅም አመታት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲታገሉ የነበሩትና በስፖርት ጋዜጠኝነት እና በአመራርነት የሚታወቁት አንጋፋው የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ
ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሥነ-ስርዓት በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገ ሽኝት
የቀብር ሥነ ስርዓተቻ ተፈጸሟል።
የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ታላቁን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን የሚዘክር ፕሮግራም በቦሌ ካሶፒያ ሆቴል የባህልና ስፖርት ሚንስቴር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ ሻለቃ አትሌት ሀይለ ገብረ ስላሴ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀልን፣እና በርካታ ጋዜጠኞችና እንግዶች በተገኙበት የመታሰቢያና የሻማ ማብራት ስርአት ተከናውኗል ።
አምባሳደር መስፍን ቸርነት: ፍቅሩ ኪዳኔ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት የመጀመሪያውና የሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች አርአያ የሆነ ነበር ከርሱ ጋር ለመመካከርና ልምዱንም ለመጋራት እመኝ ነበር ፍቅሩ ኪዳኔ የኢትዮጵያ የስፖርት ታላቅ አምባሳደር ነበር ብለዋል።
ሻለቃ አትሌት ኃይለ ገብረ ሥላሴ ፍቅሩ ኪዳኔ ኢትዮጵያን ለአለም በሚገባ ያስተዋወቀ ለኢትዮጵያ ስፖርት ጥብቅና የቆመ ሰው ነበር
እኔን ከታላላቅ የአለም የስፖርት መሪዎች ያስተዋወቀኝ ጀግናና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ነበር በማለት ስለቀረቤታቸው ሰፋ ያለ ንግግር አድርጓል።
አቶ አብነት ገብረ መስቀል በበኩላቸው የስፖርት ጋዜጠኞች የርሱን አርአያ ተከተሉ እሱ
በካፍ ለኔና ለሀገሩ ትልቅ ስራ የሰራ ጀገናና ሀገር ወዳድ የስፖርት ጀግና መሪ ነበር የቀብር ስነስርአቱ በሚወዳት ሀገሩ ቢሆን ጥሩ ነበር በማለት ንግግራቸውን እንባ ስለተናነቃቸው አቋርጠዋል።
በመታሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በህይወት ዘመናቸው የሰራቸውንና የሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልምም ቀርቧል።
በ1928 አ/ም የተወለዱት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ/ም በ87 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን በዛሬው እለት
ወዳጅ ዘመድ እና በርካታ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በፓሪስ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
ከአቶ ፍቅሩ ስራዎች መካከል
👉 የፒያሳ ልጅ የሚል መጸሀፍ በማሳተም እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን ስራ እያዋዙ በማቅረብ ተወዳጅነትን አትርፈዋል።
👉 የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላለፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ናቸው ።
👉 ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የስፖርት ዘገባዎችን አቅርበዋል
👉 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በካፍ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ በአመራርነት ሰርተዋል
ኢትዮጵያን ስፖርት በአቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ህልፈት ሀዘኑን ይገልጻል
ለመላው ስፖርት አፍቃሪያን እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
👉ፈለቀ ደምሴ