ሀገርን ቀይሮ ለሌላ ሀገር መሮጥ ያሳፍራል ወይስ ያስከብራል

ባለፉት ሰላሳ አመታት እጅግ በርካታ አትሌቶች በሀገር ውስጥ ባለ አሰራር ውዝግብ እና በአብዛኛው በሀገር ውስጥ እና ውጪ የሚገኙ የተለያዩ ደላላዎች እያስኮበለሏቸው ዜግነታቸውን በመቀየር ለተለያዩ ሀገራት እየሮጡ ትውልድ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን እየተፎካከሩ ሜዳሊያዎችን እየነጠቁ ክብሩን ወደሌላ ሀገር ወስደውታል።
ድሮ ድሮ ይህ ጉዳይ የሚታፈርበት እና የሚወገዝ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ነውር ነበር አሁን ግን ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ይመስል ሁሉን ተቋቁመው ከሚሰሩት ከኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች ይልቅ ዜግነታቸውን ለቀየሩት የተሻለ የሚያስመስሉ ነገሮች እያየን እየሰማን ነው።

ሀገራቸውን የቀየሩ ተቀናቃኞች ብዙ ገንዘብ ይከፈላቸዋል ተመልሰው ሲመጡ በክብር ተመቻችቶላቸው የፈለጉትን ያደርጋሉ ።

በፈለጉት ሚዲያ የፈለጉትን ይናገራሉ በቻይና በኮሪያ እና በተለያዩ የሰለጠኑ ሀገራት እንደከሀዲ የሚቆጠረው ዜግነትን የመቀየር እና ሀገርን ተመልሶ የመግጠም የስፖርተኞች ወግ በአፍሪካውያን ግን ሲበረታታ እየተስተዋለ ነው።

አንድ ግለሰብ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ሀገሩን ለቆ ዜግነት ሊቀይር ይችላል በተለያየ ምክኒያት ግን ኢትዮጵያዊነቱ እያንገበገበው ስራውን እና ክብሩን ትቶ ለሀገሩ ከብር ሲዋደቅ የደከመበት ሀብቱን ሲለግስ በስፋት ይታያል።

መልሶ በሙያቸው ሀገራቸውን እየተገዳደሩ ላሉ አትሌቶች የተለየ ክብር እንዲሁም የኢንቨስትመንትና የሚዲያ ከፈሬጅ በሰፊው መስጠቱ እንደ አደጉት ሀገራት እንደነ ቻይና ከሀዲ ማለቱ ቢቀር እንኳን ለተተኪው ትውልድ ጥሩ አርአያ የሆኑትን ብናበረታታ ጥሩ ነው።

ዜግነት ቀይረው ለሌላ አገር በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሮጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

1. ሲፋን ሀሰን – ኔዘርላንዳዊት ስትሆን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሁለት ወርቅና አንድ ነሀስ በማግኘት ታሪክ ሰርታለች ።

2. ቃልኪዳን ገዛሀኝ – ለባህሬን በ10 ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ አስገኝታለች ።

3. ሰላማዊት ተፈሪ – ለእስራኤል በ5 እና 10 ሺ ርቀቶች ፉክክር አድርጋለች ።

4. ብርሀኑ በለው – ለባህሬን በ5 ሺ ሜትር ሮጧል ። ጠንካራ ፉክክርም አድርጓል ።

5. ዳዊት ፍቃዱ – ለባህሬን በ5 ሺ ሜትር ውድድሩን አድርጓል ።

በአረብ እና እስያ ሻምፒዮናዎች ላይ ለባህሬን ወርቅ አስገኝቷል ። ዜግነት የቀየረው 2017 እ.ኤ.አ ላይ ነው።

6. በቀለ አለሙ – የባህሬን የማራቶን ሯጭ ነበር

7. ደቻሳ ሹሚ – ባህሬንን ወክሎ በማራቶን ሮጧል ።

8. ከተማ ለማወርቅ – ለአውስትራሊያ ዜግነት ቀይሮ ማራቶን ላይ ተወዳዳሪ ነበር ።

9.ተፈሪ ማሩ – ዜግነት ቀይሮ ለእስራኤል በማራቶን ላይ ተወዳድሯል።

10. አማረ ግርማው – ዜግነት ቀይሮ ለእስራኤል በማራቶን ላይ ሮጧል።

11. አለሜ አዕምሮ – ዜግነት ቀይሮ ለእስራኤል በማራቶን ላይ ሮጧል።

ዜግነት ቀይረው ከዚህ ቀደም ከሀገራቸው ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የነጠቁ ንአትሌቶች

1.ዘነበች ቶላ ( ማርያም የሱፍ ጀማል ) – ባህሬን
2. አበባ አረጋዊ – ስዊድን
3. ኤልቫን አብይ ለገሰ – ቱርክ እና ሌሎችም

ምንግዜም ድል ለኢትዮጵያ
👉በዚህ ጉዳይ የራስዎን ሀሳብ አስተያየት ይስጡ
👉ላይክ ሼር ያድርጉ እናመሰግናለን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.