የእንግሊዝ (ፒ ኤፍ ኤ) አሸናፊዎች ይፋ ሆነዋል።

እ.ኤ.አ በ1907 ጀምሮ መካሄድ የጀመረው አንጋፋው የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች (ፒ ኤፍ ኤ ) ሽልማት ዘንድሮም በእጩነት ካቀረባቸው ተጫዋቾች መካከል በወንዶች የሊቨርፑሉ ሞሀመድ ሳላህ በመባል ተመርጧል። ከ2017/18 የውድድር ዘመን በኋላ ይህንን ክብር ሲያገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በታሪክ  ይህንን ሽልማት ደግሞ ሁለት ጊዜ ማሳካት የቻለ 9ኛው ተጫዋችም መሆን ችሏል።

ከሞ ሳላህ ጋር በእኩል ጎሎች የወርቅ ጫማ ተሸላሚ የነበረው ደቡብ ኮሪያዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጫዋች ሶን ሁንግ ሚን በእጩነት ራሱ አለመቅረቡ እያነጋገረ እንደነበር የሚታወስ ነው።

በሴቶች ዘርፍ ደግሞ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤት ድንቅ የውድድር ዘመንን ያሳለፈችው ማለትም ባደረገችው 20 ጨዋታዎች 20 ጎል አስቆጥራ 4 ኳሶችን አመቻችታ ማቀበል የቻለችው አውስትራሊያዊቷ ሳም ኪር ኮኮብ ተጫዋች በመባል ተመርጣለች።

በወጣት ወይም ታዳጊ ተጫዋቾች ዘርፍ አጨቃጫቂ በሆነ መልኩ የማንቸስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጫዋች ፊል ፎደን በመባል ተመርጧል። ከዚ ቀደም ብሎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ታዳጊ ተጫዋች መባሉ አይዘነጋም።

በሴቶች ዘርፍ የማንቸስተር ሲቲዋ ላውረን ኸምፕ ኮኮብ ተጫዋች በመባል ተመርጣለች።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.