ዕድሜ ጠገቡ የሴኡል ማራቶን በደቡብ ኮሪያ ተካሄደ።
👉በአለም አትሌቲክስ አወዳዳሪ አካል የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠው እና የአለማችን ፈጣኑ ማራቶን እየተባለ የሚጠራው እና አንጋፋው የሴኡል ማራቶን በደቡብ ኮሪያ ተካሂዷል።
እ.ኤ.አ በ1964 ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው እና ዘንድሮ ለ76ኛ ጊዜ በተካሄደው ይህ አንጋፋ ማራቶን ላይ ኢትዮጵያዊው አትሌቶች የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር በማሻሻል አሸንፈዋል።
በየአመቱ ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፈው ይህ ውድድር ከ 2019 በኋላ በኮቪድ ወረርሽኝ መካሄድ አልቻለም።
▪️በዘንድሮው ማራቶን በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ሞስነት ገረመው የቦታውን ሰዓት በማሻሻል 2:04.43 በመግባት አሸንፏል።
▪️ሌላው ኢትዮጵያዊ ሄርጳሳ ነጋሳ 2:04:49 በመግባት 2ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።
▪️ ብራዚሊያዊው ዳንኤል ናሺሜንቶ 2:04:51 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
👉በሴቶች
▪️ሮሜንያዊቷ አትሌት ሜሊ 2:18:04 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሯን ስታጠናቅ
▪️ኢትዮጵያዊቷ ሱቱሜ አሰፋ ቀመደ 2:18:12 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
▪️ባህሬናዊቷ ፖውል ኪፕሪ 2:20:02 በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ሚካኤል ደጀኔ።