በፓሪሱ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች አስገራሚ ድል ተጎናጸፉ

በፓሪሱ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች አስገራሚ ድል ተጎናጸፉ

👉አመታዊው የሽኔይደር ኤሌክትሪክ ማራቶን በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ አስተናጋጅነት ተካሂዷል።

👉በአውሮፓ ሀገራት በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁ ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የፓሪስ ማራቶን ዘንድሮም ለ46ኛ ጊዜ ሲካሄድ ከ40,000 በላይ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎችንም አሳትፏል።

👉በሴቶቹ በተካሄደው ውድድር የ27 አመቷ ኬንያዊቷ ጁዲት ጄፕቱም የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል ጭምር 2:19:48 በመግባት አንደኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን ስታጠናቅ ኢትዮጵያን አትሌቶች ከ2 እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ፋንቱ ጅማ 2:22:52
በሱ ሳፖ 2:23::16
አዳነች አንበሴ 2:24:07
እንዲሁም የነሳሽ ድንቄሳ 2:24:09 በመግባት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

👉በወንዶቹ ዘርፍ ጫሉ ገልሜሳ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሰይፉ ቱራን በቅርብ ርቀት በማስከተል 2:05:07 በመግባት ቀዳሚ ሲሆን የገባበት ሰአት በታህሳስ ወር በቫሌንሺያ ካስመዘገበው የግል ምርጥ ሰአቱ 9 ሰከንድ ያሻሻለበት ነው። የካሊፎርኒያ ማራቶን አሸናፊው ሰይፉ ቱራ 3 ሰከንዶችን በመዘግነት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል። ፈረንሳዊው ሞራድ አብዱኒ 2:05:22 በመግባት 3ኛ ደረጃን ሲይዝ ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን አባይነህ ደጉ እና ኦሊካ አዱኛ 4ኛ አሰና 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.