በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል አመታዊው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኬኒያውያኑ አሸናፊ ሆነዋል
በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል አመታዊው የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሂዷል
▪️እ.ኤ.አ በ1987 ጀምሮ መካሄድ የጀመረው ይህ ማራቶን ውድድር በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ አወዳዳሪ አካል አይ ኤ ኤፍ የወርቅ ደረጃ ተሰጥቶታል።
▪️በሴቶች በተካሄደው ውድድር የአለም የሀገር አቋራጭ እንዲሁም የ2 ጊዜ የአለም የ5,000 ሜትር ሻምፒዮኗ ሄለን ኦቢሪ የግሏን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ በአንደኝነት ውድድሯን አጠናቃለች።የ32 አመቷ ኬንያዊት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1:04:48 ሰከንድ ፈጅቶባታል።
▪️አምና በኮፐንሀገን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የግሏን ምርጥ ሰአት 1:05:08 በማስመዝገብ ያጠናቀቀችው የ23 አመቷ ፀሀይ ገመቹ 1:05:52 በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት በቀለች ጉደታ 1:06:35 በመግባት 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
▪️በወንዶቹ ከ1-3 ያለውን ደረጃ ኬንያውያን ተቆጣጥረውታል። ሮጀርስ ኪዎምቢ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 59:15 ሲፈጅበት ዳንኤል ማቲዬኮ 1:00:05 በመግባት 2ኛ እንዲሁም ከ15 ሰከንድ በኋላ ኢማኑኤል ቦር 1:00:20 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
