በስፔን ሲቭያ የተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያን ድል ቀንቷቸዋል።

▪️እ.ኤ.አ ከ1985 ጀምሮ በሲቭያ ጎዳናዎች መካሄድ የጀመረው ይህ ማራቶን ዘንድሮ ለ 37ኛ ጊዜ በስፔን ሲቭያ ከተማ ተካሂዷል። በሴቶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር አለሙ መገርቱ የግሏን ምርጥ ሰአት 2:18:51 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሯን ስታጠናቅ ባሳለፍነው አመት ህዳር ወር በባርሴሎና 2:24:09 እንደ ምርጥ የግል ሰአቷ ሆኖ የተመዘገበላት መሰረት ጎላ 2:21:10 በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የግሏን ምርጥ ሰአትም ማሻሻል ችላለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊ ካላዩ ቸኮል 2:21:17 በመግባት 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

▪️በወንዶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር ጥሩ ፉክክር የታየበት ሲሆን ኢትዮጵያዊው አስራር አብዱራህማን 2:04:43 በመግባት በአንደኝነት ውድድሩን ሲያጠናቅቅ የቦታውንም አዲስ ሪከርድ ማስመዝገብ ችሏል። በዚህ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካፈለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አደላድለው ማሞ 2:05:12 በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዟል። የ2015 የአለም አትሌቲክስ አሸናፊው ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገ/ስላሴ  አደላድለው ከገባበት ሰአት 22 ሰከንዶች በመዘግየት 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.