በናይጄሪያ ሌጎስ በተደረገው ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አመርቂ ድል ተጎናፀፉ።
▪️በናይጄሪያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚዘጋጀው እና የሲልቨር ደረጃ የሚሰጠው ማራቶን ውድድር በናይጄሪያ ሌጎስ ተካሂዷል። ውድድሩ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በሁለቱም ፆታዎች ውድድሩን አካሄዷል።
▪️በወንዶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ገለታ ኡልፋታ ከ300 በላይ የሚሆኑ አትሌቶችን በመቅደም በአንደኝነት አጠናቋል። 42 ኪሎ ሜትሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰአት ከ11 ደቂቃ 54 ሰከንድ የፈጀበት ሲሆን 30,000 የአሜሪካ ዶላርም ተሸላሚ ሆኗል። ኬንያውያኑ ዴቪድ ባርማሳይ እና ኢማኑኤል ናቤዪ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል። የ20,000 እና የ15,000 ዶላር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
▪️በሴቶች የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ስራነሽ ይርጋ በአንደኝነት ውድድሯን አጠናቃለች። ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰአት ከ33 ደቂቃ 50 ሰከንድ ፈጅቶባታል። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አለምነሽ ጉታ 2ኛ እንዲሁም ኬንያዊቷ ናኦሚ ማዮ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በ2019 በተካሄደው እና ከ100,000 በላይ አትሌቶችን አሳትፎ የነበረው ይህ የሌጎስ ማራቶን ላይ በወንዶች ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ለገሰ 2ሰአት ከ17 ደቂቃ 28 ሰከንድ በሴቶች ደግሞ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ድንቄ መሰረት በአንደኝነት ማጠናቀቋ ይታወሳል ከዛን ጊዜ ወዲህ በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን ሲያሸንፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ፈለቀ ደምሴ።