የሲንኬ ሙሊኒ ሀገር አቋራጭ ውድድር።
▪️ይህ የሲንኬ ሙሊኒ አመታዊ የሀገር አቋራጭ ውድድር ዘንድሮም በጣልያን ተካሂዷል። ለ90ኛ ጊዜ ውድድሩ ሲካሄድ የወርቅ ደረጃ ከተሰጣቸው የሀገር አቋራጭ ውድድሮች መሀከል አንዱ ነው።
▪️በወንዶች በተካሄደው ውድድር ንብረት መላክ በአንደኝነት ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል። የአማራ ማረሚያ ስፖርት ክለብ አባል የሆነው እና በኮማንደር ሁሴን የሚሰለጥነው ንብረት መላክ የውድድሩ የመጨረሻ ዙሮች ላይ ፍጥነቱን በመጨመር ማሸነፍ ችሏል።
▪️እሱን በመከተል ኬንያዊው ሌቪ ኪቤት 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ የአለም ከ 20 አመት በታች የ 3ሺ ሜትር ሻምፒዮኑ ታደሰ ወርቁ 3ኛ ሆኖ አጠናቋል። ኢትዮጵያ ሲንኬ ሙሊኒውን ሀገር አቋራጭ ውድድር 17 ጊዜ በማሸነፍ በቀዳሚነት ምትመራ ሀገር ናት።
▪️በሴቶች ኬንያዊቷ ቴሬሺያ ጋቴሪ በአንደኝነት ውድድሯን ስታጠናቅ ሌላዋ ኬንያዊት ዜናህ ዬጎ ከ5 ሰከንድ በኋላ ተከትላ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ስሎቬናዊቷ ክላራ ሉካን 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ፈለቀ ደምሴ።