ጉዳፍ ፀጋዬ ዘንድሮ የሚካሄደውን የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ሪከርዷን ታሻሽል ይሆን?
▪️ጉዳፍ ፀጋዬ የፊታችን የካቲት 9 በፈረንሳዩ ሊዬቪን ከተማ የሚካሄደው የአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድሮች እንደምትሳተፍ ታውቋል። የ24 አመቷ ጉድፍ ፀጋዬ ባሳለፍነው አመት በተካሄደው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር በ 1500 ሜትር 3:53:09 በመግባት እና በ2014 በጀርመኗ ካርልስሩ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ከገባችበት ሰአት 2 ሰከንዶችን አሻሽላ የአለም ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች።ከዛም በሳምንቱ በ 800 ሜትር የግሏን ምርጥ ሰአት ማለትም 1:57:52 በመግባት ማጠናቀቋ እና አመቷን ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በማግኘት አጠናቃለች።
▪️ይህ የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር አምና ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረጉትን በ 1500 ሜትር ኖርዌያዊው jakob ingebrigsten እና በ 3000 ሜትር ኢትዮጵያዊ ጌትነት ዋሌ ጨምሮ የ100 ሜትር የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱን ጣልያናዊው ማርሻል ጄኮፕሰን ጨምሮ ሌሎችም በውድድሩ ምንመለከታቸው አትሌቶች ናቸው።
ፈለቀ ደምሴ