ቤን ቺልዌል ያጋጠመው ጉዳት እስከመች ከሜዳ ያርቀው ይሆን?
▪️የቼልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ቤንጃሚን ቺልዌል ህዳር 14 ጁቬንቱስን በሻምፒዮንስ ሊጉ 4-0 ሲያሸንፉ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።ጉዳቱ anterior cruciate ligament damage በተለምዶ ACL እየተባለ ሚጠራው ጉዳት ነው ያጋጠመው። ቺልዌል በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዲሁም ቼልሲም ቀለል ያለ ጉዳት እንደሆነ እና ቶሎ ወደ ልምምድ እንደሚመለስ ነበር ግምታዊ ሀሳባቸውን የገለፁት ግን ቁርጭምጭሚቱ ጋር ቀዶ ጥገና እንዲደረግ ዶክተሮች ወስነው ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ግን መጥፎ ዜና ለቼልሲ ደጋፊዎች የሆነባቸው ዘንድሮ ቺልዌልን ሜዳ ላይ በቼልሲ ማልያ ዳግም ማየት ማይታሰብ ነገር እንደሆነ እና ቀሪው የውድድር ዘመንም ወደ ሜዳ መመለስ እንደማይችል ተገልጿል።

▪️ቺልዌል ከመጎዳቱ በፊት ለቼልሲ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ተጫዋች ነበር። ዘንድሮ ብቻ በፕሪሚየር ሊጉ 6 ጨዋታዎችን ሲያደርግ 3 ጎል እና 1 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ቶማስ ቱኸል በሱ ቦታ ማርኮስ አሎንሶን እየተጠቀሙ ቢገኙም ከቺልዌል ሚያገኙት የነበረውን ግልጋሎት ከዚህ ስፔናዊ ተጫዋች እያገኙ አለመሆኑ እና ሌላው የግራ መስመር ተከላካያቸው ጣልያናዊው ኤመርሰን ፓልሜሪ በውሰት ወደ ሊዮን በማምራቱ እና ቱኸል የዚህን ተጫዋች ግልጋሎትንም ስለማይሹ በጥር የዝውውር መስኮት የግራ መስመር ተከላካይ የሆነ ተጫዋች ለማምጣት ወደ ገበያ ሊወጡ ይችላሉ ሚሉ ዜናዎችም እየተበራከቱ ይገኛሉ።
ሚካኤል ደጀኔ።
