125ኛው የቦስተን ማራቶን ዛሬ ተካሄደ።
▪️ረጅመም እድሜን ካስቆጠሩ ማራቶኖች መሀከል በግንባር ቀደምትነት ሚጠቀሰው የ ቦስተን ማራቶን ከ 900 ቀናቶች በኋላ ዛሬ ተካሂዷል።
▪️ባሳለፍነው አመት 2020 በ ኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው ይህ ማራቶን ዘንድሮ አስፈላጊውን የ ኮቪድ ህግና ደንቦች ተግባራዊ በማድረግና ተወዳዳሪዎች ውድድሩ ከመካሄዱ 72 ሰአት በፊት በሚደአገው ምርመራ የኔጌቲቭ ውጤት መሳየት ይጠበቅባቸዋል።
▪️ዳጎስ ያለ ሽልማትን ሚያዘጋጀው ይህ ማራቶን እስከ 20,000 ሚጠጉ አትሌቶችን አሳትፏል።
▪️በወንዶች ኬንያዊው ቤንሰን ኪፕሩቶ 2 ሰአት ከ9 ደቂቃ ከ 51 ሰከንድ በ አንደኝነት ውድድሩን ሲያጠናቅቅ
▪️ለሚ ብርሀኑ እና ጀማል ይመር ከ ኢትዮጵያ 2:10:37 እና በ 2:10:38 በ 1 ሰከንድ ተለያይተው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
▪️በሴቶች ኬንያውያን ደምቀው ነበር ከ 1-3 ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
▪️ዲያና ኪፕዮጊ በ 1ኝነት ስጨርስ 2:24:45 ሰከንድ ፈጅቶባታል። አደን ኪፕላጋት 2:25:09 ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ ከ11 ሰከንድ በኋላ ማሪ ንጉጊ 2:25:20 3ኛ ሆና አጠናቃለች።
▪️ኢትዮጵያዊቷ ነፃነት ጉደታ 2:26:09 በመግባት የ ቦስተን ማራቶኑን በ 5ኛ ደረጃነት አጠናቃለች።
ሚካኤል ደጀኔ።