የቺካጎ ማራቶን አስደናቂው ድል።
▪️43ኛው የ ቺካጎ ውድድር በሀገረ አሜሪካ Illinois ግዛት የተካሄደ ሲሆን እስከ 55,000 አትሌቶች ተሳትፈውበታል።
▪️በአለማችን የማራቶን ደረጃ 3ኛ ላይ የሚገኘው ይህ ማራቶን አምና በ2020 በ ኮቪድ ተፅእኖ ምከሰንያት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወሳል።
▪️በዘንድሮው ውድድር ተሳታፊ ከሆኑ ኢትዮጽያውያን አትሌቶች መሀከል በወንዶች የ24 አመቱ ሰይፉ ቱራ አሸናፊ ሆኗል 26.2 ማይል ርቀት የነበረውን ይህ ማራቶን ለማጠናቀቅ ሰይፉ 2:06:12 ሰከንድ ፈጅቶበታል።
▪️አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ 2ኛ ሆኖ በ 2:06:35 ሰከንድ ሲጨርስ ኬንያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ በ 2:06:51 ሰከንድ 3ኛ ሆኖ አጠናቋል።
በሴቶች
▪️ኬንያዊቷ ሪፕ ኬፕ ጌቲች 2:22:31 በሆነ ሰአት ቀዳሚ ስትሆን አሜሪካዊቷ ኤማ ቤትስ በ 2:24:20 ሰከንድ 2ተኛ ሆና አጠናቃለች።
▪️በተመሳሳይ ሰአት በተደረገ ወንዶች የዊልቼር ማራቶን ውድድር ዳንኤል ሮማንቹክ በ1:29:07 ሰከንድ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ በሴቶች ታቲያና ማክፋደን በ 1:48:57ሰከንድ በ1ኝነት አጠናቃለች።
ሚካኤል ደጀኔ