ሊዮኔል ሜሲ ባርሳን ወደ ድል መልሷል
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፈታኝ በነበረው ጨዋታ ሪያል ቤቲስን 3 ለ 2 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከሜዳቸው ውጪ አሳክተዋል ።
• ሜሲ ተቀይሮ በገባ 136 ሴኮንድ ግብ በማስቆጠር ፈጣኑን ጎል አስቆጥሯል ።
• ሜሲ በላሊጋው ታሪክ ተቀይሮ በመግባት ሀያ ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ሁለተኛው ተጫዋች ሲሆን ከእርሱ በላይ ጁሊዮ ሳሊናስ በ ሀያ ስምንት ጎሎች ተቀምጦ ይገኛል ።
• ባርሴሎና በላሊጋው በተጋጣሚ ተጫዋቾች አራት ጎሎች ተቆጥረውላቸዋል ።
• ሜሲ ከ ሪያል ቤቲስ ጋር ባደረጋቸው ሀያ ጨዋታዎች ሀያ ስድስት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።
• ቤቲስን መሪ ያደረገችውን ግብ ማስቆጠር የቻለው ቦርጃ ኢግሌሲያስ ባለፉት 182 ደቂቃዎች አራት ጎሎችን አስቆጥሯል ።
• በዚህ ጨዋታ የባርሴሎናው የመሐል ተከላካይ ሮናልድ አራውጆ ከበድ ያለ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ከሜዳ ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል ።
• ሊዮኔል ሜሲ በውድድር ዓመቱ በላሊጋው አስራ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።
• ባርሴሎና ካለፉት አስር ጨዋታዎች በአምስትቱ ሶስት እና ከዚያ በላይ ጎሎችን በተጋጣሚ ላይ በማስቆጠር አሸንፈው ለመውጣት ችለዋል ።
• የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግብ ማስቆጠር የቻለው ትሪንካኦ ለባርሴሎና በላሊጋው የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል ።
• ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና የሁለተኛ ቦታን ከ ሪያል ማድሪድ መረከብ ችለዋል ።
