ኢትዮ ቴሌኮም የአዳማና አካባቢው የኤሌትሪክ መኪና ተጠቃሚዎችን ጥያቄ መለሰ!
በአዳማ ከተማ ደራርቱ አደባባይ ወደ ወለንጪቲ በሚወስደው መንገድ ላይ የገነባውን አራተኛውን እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ በይፋ ስራ አስጀምሯል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋነና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት በአራተኛው ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ሥራ የገባው ይህ የኤሌትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ እና እጅግ የላቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀምና በተለይም የአውሮፓ እና የቻይና ስሪት ለሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (European EV Models) ጭምር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለው ዋና ሰራ አሰብ ፈጻሚዋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ይህ በአዳማ የተገነባው የኤሌትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያ ከተሽከርካሪዎቹ ዓይነት ጋር ራሱን የሚያጣጥም እጅግ ፈጣን (Super-Fast) ኃይል መሙያ የተገጠመለት ሲሆን እነዚህ ቻርጅ ማድረጊያዎች 12 እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኃይል መሙያዎች እያንዳንዳቸውና እስከ 180 ኪሎዋት በሰዓት የሚደርስ የመሙላት አቅም እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋነና ስራ አስፈጻሚ በእለቱ እንደገለጹት ኢትዮ ቴሌኮም እጅግ ፈጣን የሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ከመገንባት ባለፈ፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የገነቧቸው ጣቢያዎች በተቀናጀ የዲጂታል ስነ-ምህዳር ውስጥ እንዲካተቱ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ፕላትፎርም አዘጋጅቷል ብለዋል። በዚህም፦ የግልም ሆነ የመንግስት ድርጅቶች የኤሌትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ሲገጥሙ ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ማበረታታት እና ማገዝ ስለሚፈልግ አፕሊኬሽን ለማዘጋጀት ወይም ለመገንባት መድከም የለባቸውም ኢትዮ ቴሌኮም ባዘጋጀው የቻርጂንግ ፕላትፎርም መጠቀም ይችላሉ ብለዋል። በዚህ የተቀናጀ አሰራርም ተጠቃሚዎቻቸው እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ጣቢያዎች ሁሉ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል አገልግሎት ያገኛሉ በማለት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በሰፊው አብራርተዋል።

የአዳማና ከተማው ከንቲባዎች ኃይሉ ጀልዱ ኢትዮ ቴሌኮም ስላስገነባው የኤሌትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ምስጋናቸውን አቅርበው ስለአዳማ ከተማ ስማርት ፕሮግራም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚሁ የኤሌትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ የምርቃት ስነስርአት ላይ ኢትዮ ቴሌኮም የተመሰረተበትን 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ‘ሜጋ ፕሮሞ’ እድለኛ ለሆኑ አራት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ርክክብ አከናውኗል።

የመጨረሻውን ዙር ሽልማት ደግሞ በአዳማ ከተማ ያካሄደ ሲሆን በዚህም ተቋሙ ለባለ ዕድለኞች አራት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች አስረክቧል።

በመርሐ ግብሩ እስካሁን 12 የኤሌክትሪክ መኪናዎች እና 13 ባጃጆችን ለባለ ዕድለኞች ማስረከቡን ኢትዮ ቴሌኮሞ አሳውቋል።
ፈለቀ ደምሴ
