51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና።
ይህ የትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ1963 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ አንጋፋ ውድድር ሲሆን ዘንድሮም ለ51ኛ ጊዜ ከመጋቢት 19-24 በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ለ6 ቀናት ይካሄዳል።
▪️ከ7 ክልሎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም 24 ክለቦችና ተቋማት የተወጣጡ 1033 አትሌቶች እንደሚሳተፉበት ታውቋል። ይህ ውድድር እነ ጀግናው ሻምበል አበበ ቢቂላ ፣ ማሞ ወልዴ ፣ ምሩፆ ይፍጠር ፣ ሀይሌ ገ/ስላሴ ፣ ቀነኒሳ በቀለ ፣ በሴቶቹ እነ መሠረት ደፋር፣ አልማዝ አያና ፣ ጥሩነሽ ዲባባ ፣ ማሬ ዲባባ ፣ ጨምሮ በኦሎምፒክ መድረኩ በርካታ ድሎችን ያስመዘገቡ አትሌቶችን ያፈራ ነው። ዘንድሮ የሚካፈሉ አትሌቶችን ለመጥቀስ ያክል
▪️በሴቶች ያለምዘርፍ የኋላ ፣ ብርቱካን አዳሙ ፣ ሀብታም አለሙ ፣ እጅጋየሁ ታዬ
▪️በወንዶች ሙክታር አሰድሪስ ፣ ተስፋሁን አካልነው ፣ ቦኪ ድሪባ የሚሳተፉ ይሆናል።
▪️ከአዲስ አበባ ውጪ ሲካሄድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ የውድድሩ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ውድድሩ በተሻለ ሁኔታ እንዲመራ በዳኞች በኩል ትኩረት ተደርጎ እንደተሰራ እና በወርልድ አትሌቲክስ ደረጃ ኮርስ የወሰዱ ዳኞች መመደባቸውን በማስታወስ ለውድድሩ አሸናፊዎች የገንዘብ እንዲሁም የሜዳሊያ ሽልማቶች እንደሚበረከት ገልፀዋል። በየውድድሩ
1ኛ ለሚወጣ 3,500
2ኛ ለሚወጣ 2,500
3ኛ ለሚወጣ 2,000 ብር እንዲሁም በአጠቃላይ የሴትና የወንድ አሸናፊ
1ኛ ለሚወጣ 22,000 ብር
2ኛ ለሚወጣ 17,000 ብር
ሪከርድ ላሻሻሉ 7,000 ብር
3 ወርቅ ላስመዘገቡ 7,000 ብር
2 ወርቅ ላስመዘገቡ 6,000 ብር
በአጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት መጠኑ 541,000 ብር እንደሆነ ተገልጿል።
▪️ይህ ውድድር በሰኔ ወር በሞሪሽየስ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤታማ አትሌቶች የሚታዩበት እንዲሁም ከሁለት ወራት በኋላ በአሜሪካ ኦሬገን በሚካሄደው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፐመዮና ውጤታማ አትሌቶችን ለመለየት ታስቦ የሚካሄድ ውድድር መሆኑ ተገልጿል።
▪️ዋልታ ቴሌቪዥን ውድድሩን በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ታውቋል።
▪️የፆህፈት ቤቱ ተወካይ አቶ ዮሀንስ እንግዳ እንዲሁም የውድድሩ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ከሚዲያ አካላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።
▪️ለተወዳዳሪዎች ለሚበረከተው ገንዘብ ማነስ ለተጠየቁት ጥያቄ ፌዴሬሽኑ 41 የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እንደሚያካሄድ በመግለፆ በየዘርፉ ከዚ በላይ የገንዘብ ሽልማት ማበርከት በጀቱን እንደሚያሳሳው ግን የገንዘብ ሽልማቱ በቂ ነው ብሎ እንደማያስብ ገልጿል። ስፖንሰሮች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፎ ቢያደርጉ የገንዘብ መጠኑ ሊሻሻል እንደሚችል ጠቁመዋል።
▪️ከኮቪድ ጋር ተያይዞ ለቀረበው ጥያቄ ሁሉም አትሌቶች የኮቪድ ህግና ደንብን በጠበቀ መልኩ ውድድር እንደሚያካሄዱ እና ሁሉም አትሌቶች የኮቪድ ምርመራ ወረቀትን ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ፌዴሬሽኑ በጥብቅ እንደሚያሳስብ አስታውቀዋል።
