ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በባርሴሎና ክብረ-ወሰን ጭምር በማሻሻል አሸነፉ።
▪️ኢትዮጵያዊያኑ እጅጋየሁ ታየ እና በሪሁ አረጋዊ በ cursa dels nassons ባርሴሎና የተካሄደውን የ 5 ኪሎሜትር የሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታ የአለምን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል አመርቂ ውጤትን አስመዝግበዋል።
▪️የ21 አመቷ እጅጋየሁ ታየ የአመቱ መጀመሪያ አካባቢ በ3000 ሜትር 8:19:52 መግባቷ ይታወሳል። ዘንድሮም በ5000 ሜትሩ 2ተኛ ፈጣኗ ሴት ተብላም ነበር። እጅጋየሁ በሩጫ ህይወቷ የጎዳና ላይ ሩጫ ስትሮጥ ይህ ለ2ኛ ጊዜዋ ብቻ ቢሆንም በባርሴሎና ሪከርድ በማሻሻል ጭምር 14:19 በመግባት ድልን መጎናፀፍ ችላለች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ግን በዜግነት ስዊድናዊ የሆነችው ምዕራፍ ባህታ 2ኛ ስትሆን ስፔናዊቷ አትሌት ካርላ ዶሚኒጌዝ 3ኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።

▪️የ 20 አመቱ በሪሁ አረጋዊ ባሳለፍነው ወር በኬንያዊው ጆሺዋ ቼፕቲጊ የተያዘውን የአለም ሻምፒዮና ሪከርድ ለማሻሻል ከጫፍ ደርሶ ነበር። የዳይመንድ ሊጉ አሸናፊ በሪሁ አረጋዊ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 12:49 የፈጀበት ሲሆን የቼፕቲጊ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ 2 ሰከንድ አሻሽሎታል።ኬንያዊው ፒተር ማሩ 2ኛ እንዲሁም ኔዘርላንዳዊው ማይክ ፎፐን 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ፈለቀ ደምሴ
