አርሰናል ከባዱን ጨዋታ በድል ተወጥቷል

በአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረጉትን የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲን ኦዴጋርድ እና ፋብያን ሼር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል ።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰማንያ አንድ በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።

ኒውካስል ዩናይትዶች በስልሳ አምስት ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከብራይተን እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ይገናኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.