በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የጊኒ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ ላይ መግለጫ ተሰጠ

👉በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የጊኒ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ አስቀድሞ የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ የተደረገ ሲሆን በስብሰባው ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ከቤኒን እንዲሁም ኮሚሽነር ከቡርኪና ፋሶ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በጨዋታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቢጫ ማልያ ፥ ቀይ ቁምጣ እና ቢጫ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል። ተጋጣሚያችን ጊኒ ደግሞ ቀይ ማልያ ፣ ቢጫ ቁምጣ እና አረንጓዴ ካሶተኒ በመልበስ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ታውቋል ጨዋታው አርብ ምሽት በኢትዮጵያ ሰአት 5፡30 ላይ ካዛብላንካ በሚገኘው መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ይደረጋል።

👉አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ቅድመ ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል

👉በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አርብ ምሽት 5:30 ላይ ከጊኒ አቻው ጋር በካዛብላንካ መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

“👉 ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገን ዝግጅት ስናደርግ ቆይተናል። የአቋም መፈተሻ ጨዋታም ከሩዋንዳ ጋር አድርገናል።
👉አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች በስብስባችን ይዘናል። በጉዳት ያጣናቸው ተጫዋቾች ቢኖሩም የተተኩት ተጫዋቾች እያሳዩት ያለው ነገር ጥሩ ነው።
👉በልምምድ ተጫዋቾቼ ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። ” በማለት መግለጫውን የጀመሩት አሰልጣኝ ውበቱ ተጋጣሚያቸው ጊኒን ለመገምገም እንደሞከሩ የገለፁት ሲሆን በምድቡ ቀላል የሚባል ጨዋታ እንደሌለ በመጠቆም ለሁሉም ቡድን ወሳኝ የሆነ ወቅት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ከወሳኞቹ ጨዋታዎች ውጤት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

👉ቡድኑ በወጥነት ለረጅም ጊዜያት ጥሩ ነገር እያሳየ ነው ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ ” የምዕራብ እና የሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን ስንገጥም ከዚህ ቀደም የነበረንን ሪከርድ ለማሻሻል እየሞከርን ነው።
👉በዚህ ማጣርያ ውድድር በማላዊ 2ለ1 ስንሸነፍ የነበረን እንቅስቃሴ ግብፅን ስናሸንፍ ከነበረው ብዙ የተለየ አልነበረም። በአጠቃላይ ግን ቡድኑ ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ያለው።”
ብለዋል።

👉ከማጥቃት ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ የአጥቂ ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ እንዳልሆነ ገልፀው እንደ ቡድን ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

👉አምበሉ ሽመልስ በቀለ በበኩሉ ስብስቡ ከበፊቱ በተሻለ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አውስቶ እዚህ የተገኙት ነጥብ ለማሳካት እንደሆነ በመጠቆም በአሠልጣኞች ቡድኑ እና የቡድን አጋሮቹ ሙሉ እምነት እንዳለው በመጠቆም ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ተናግሯል።
👉አማካዩ በተጋጣሚ ቡድን ውስጥ ስለሚገኘው ናቢ ኬታ ተጠይቆም ለማንም የተለየ ትኩረት እንደማያደርጉና አንድ ተጫዋች ብቻ ሳይሆን እንደ ቡድን ግብፅን የመሳሰሉ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድኖች ገጥመው እንደነበር በማንሳት ከጨዋታው የተሻለ ነገር ለማምጣት እየተዘጋጁ እንደሆነ አምላክቷል።

በጨዋታው ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሁለት ቢጫ ቅጣት ምክንያት ከሚያመልጠው ምኞት ደበበ ውጪ ሁሉም ከጉዳት እና ቅጣት ነፃ እንደሆኑ ተገልጿል።

👉መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.